(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ የ10 አመት የእስር ትዕዛዝ ተላለፈባቸው። ፍርድ ቤቱ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ውሳኔውን ያሳለፈው ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም የሃገሪቱን ገንዘብ መዝብረዋል በሚል ነው። ተዘረፈ በተባለው ገንዘብም በለንደን አራት የቅንጦት መኖሪያ ቤቶችን መግዛታቸውንና ከህዝብ…

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010)በሃዋሳ ከተማ ከተነሳው ግጭት ጋር በተያያዘ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ። የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሉሉ አዱላና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴድሮስ ገቢባ በከተማዋ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ ከትላንት ሰኔ 28/2010…

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) በኢትዮጵያ የኢሕአዴግ መርህ እየተተወና ፈላጭ ቆራጭ አመራር እያደገ መጥቷል ሲሉ የሕወሃት አመራሮች ገለጹ። የሕወሃት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልና የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አለም ገብረዋህድ ከክልሉ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ውይይትም…
በሶማሌ ክልል እስረኞችን ማሸሽ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010)የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ እስረኞችን በማሸሽ ላይ መሆኑ ተገለጸ። ከፍተኛ ሰቆቃ የሚፈጸምበት ጄይል ኦጋዴን ዛሬ ከ20 አዳዲስ እስረኞች በቀር በሺዎች የሚቆጠሩ ግፍና ስቃይ የደረሰባቸው እስረኞች በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች ወደሚገኙ እስርቤቶች እንዲሸሹ…

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) በምዕራብ ጎጃም የቻግኒ ከተማ ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ አደረገች። የድጋፍ ሰልፉ በዳውሮና በሌሎችም የደቡብ ክልል አካባቢዎች መካሄዱ ታውቋል። አርባምንጭ ለነገው የድጋፍ ሰልፍ የሚደረገውን ዝግጅት የከተማዋ አመራር እያደናቀፈ መሆኑ ተገለጿል። በውጭ ሀገራትም በኢትዮጵያ የሚታየውን የለውጥ ጅምር በመደገፍ ሰልፎች መካሄዳቸውን…
የተፈጠረውን ሁኔታ ለማደፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎች የትም አይደርሱም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማደፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎች የትም የማይደርሱ፣መንግስት የሚያውቃቸውና የሚቀጣቸው ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። እነዚህ ርምጃዎች ባዶ ፍላጎቶች እንጂ ለውጥን ማቆም የሚችሉ አይደሉም ብለዋል። በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ዛሬ…

አሁን የሚታዩት ግጭቶች ለውጥ ማቆም የሚችሉ አይደሉም ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትሩ በ2011 ረቂቅ በጀት ላይ ለመወያየት ፓርላማ ተገኝተው ከአባላቱ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት መልስ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማድፍረስ እዚህም እዛም ሙከራዎች ቢኖሩም፣ የትም…

ያኮረፉ የኦህዴድ አባላት ለውጡን ለመቀልበስ ከሚንቀሳቀሱት ሃይሎች ጋር ጥምረት ፈጥረው እየሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ኦህዴድ ግጭት በመፍጠር፣በሙስናና በህዝቡ ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ያባረራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ አባላች፣ የለውጡን እንቅስቃሴ…

ኦነግ በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ የሚካሄደውን ጦርነት ህዝቡ እንዲያከሽፈው ጠየቀ ድርጅቱ አቶ ለማንና ዶ/ር አብይንም አውግዟል (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ባወጣው መግለጫ በቄለም ወለጋ ውስጥ “ ለምን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እንቅስቃሴን ትደግፋላችሁ?” በማለት የጦር…

የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች 700 ሜትር ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን ገለጹ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች በባህርዳር ከተማ ተይዞ የተወጣውን ባንዲራ የሚበልጥ ረጅም ባንዲራ በመያዝ ዶ/ር አብይ አህመድ እያደረጉ ላሉት የለውጥ እንቅስቃሴ ድጋፉን ገልጿል።…

ዘይኑ ጀማል፤ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፤ ሰኔ 16 በመስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦምብ ጥቃት ምርመራ ሂደትና ሕዝባዊ ፖሊስ የማዋቀር ራዕያቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።