በደስታዉ ሙላቴ በሪፖርተር ጋዜጣ፣በተለያዩ ድህረ ገፆች እና በአንዳንድ የኤፍ ኤም(fm)ማሰራጫ ጣቢያዎች 40 እና ከአርባ በላይ የሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ የታጠቀ ሀይል መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በክልሉ ፖሊስ ሃይል በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ለህብረተሰባችን ያሰራጩት መረጃ…

በሶማሌ ክልል በዋና ከተማው ጂግጂጋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የተፈፀመው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ እንደነበር ከከፍተኛ ድብደባ በኋላ በሕክምና የተረፉት የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ገለፁ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገረስብከት በጂጂጋ ምስራቀፀሐይ ኪዳነምሕረት ካቴድራል አስተዳዳሪ መላከፀሐይ አባገብረፃዲቅ ደባብን አነጋግረናቸዋል።

ዐሥራ አምስት አባላት ያሉት የዴያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አባላት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ጥሪ ተቀብለው በበጎ ፈቃደኝነት ለማገልገል የተሰባሰቡ እንደሆኑ የአማካሪ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም አስታወቁ።

ኦህዴድና ትህነግ በማን ላይ ተስማሙ? (ጌታቸው ሺፈራው) ~በእነ አብይ መንግስት ላይ ግንባር ቀደሙ አማፂ ትህነግ/ህወሓት ነው። ለዚህ ስራው የቀን ጅብ የሚል ስም ተሰጥቶታል። ከወንጀሉ ሁሉ በስተጀርባ አለበት እየተባለ ነው። ዶክተር አብይ አህመድ በሚኒሶታ ለተነሳለት ጥያቄ ከአንዲት ከሁለት የትግራይ ተወላጆች የተነሳለትን…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) በዋሽንግተን ዲሲ ትላንት በነጭ አክራሪዎች የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው። ከ30 የማይበልጡ ስብስቦችን የያዘው የነጭ አክራሪ ቡድን በጠራውን ሰልፍ ተከትሎ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወተዋል። ባለፈው አመት በተመሳሳይ በቻርለስ ቬት ቨርጂኒያ በተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ…

(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 7 /2010) አቃቤ ህግ የሰኔ 16ቱ ቦንብ በፈነዳበት ጊዜ ክፍተት አሳይተዋል በሚል የታሰሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የነበሩትን ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ገለፀ፡፡ ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል…
ግሎባል አልያንስ ለደቡብ ክልል ተፈናቃዮች ድጋፍ  አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (ግሎባል አልያንስ) ለደቡብ ክልል ተፈናቃዮች የግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ  አደረገ። ከኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን  ለተፈናቀሉት የጌዲዮ ተወላጆች  እንዲሁም  በሐዋሳና ጉራጌ ዞን በተፈጠረው ግጭት  ለተፈናቀሉት ዜጎች  የተላከው ድጋፍ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አማካይነት  ለተፈናቃዮቹ መድረሱን መረዳት…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) በአዲስ አበባ መስተዳድር ለረጅም አመታት በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ የነበሩ ሁለት የሕወሃት አባላት ከሃላፊነታቸው ተነሱ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ እንዲሁም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ በመሆን ከ10 አመታት በላይ በስልጣን ላይ የቆዩት ሁለቱ ግለሰቦች ከስልጣናቸው የተነሱት…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010)የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታወቀ። የግንባሩ አመራሮችም በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ሃገር ቤት ገብተዋል። እስከዛሬ ድረስ በግንባሩ ስም ተደርጉ ከተባሉ ስምምነቶች በተለየ ይህንን ውሳኔ ግንባሩ በራሱ ድረ ገጽም ይፋ ማድረጉ ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ያቀረቡትን የሰላም…
በሻሸመኔ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) በሻሸመኔ ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ እንደተናገሩት በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት እጃቸው ያለበትን አካላት በመያዝ ለፍርድ ለማቅረብ ሂደቱ ተጀምሯል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) ከጅቡቲ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ። በአብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ጥቃትን ሸሽተው የተሰደዱ መሆናቸው ታውቋል። በምዕራብ ሀረርጌ አሰቦት በትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙት የጅቡቲ ተፈናቃዮች ምግብና ውሃ አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ…