መጪው አዲስ አመት ‘አንድ ሆነን አንድ እንበል’’በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለፀ ።

መጪው አዲስ አመት ‘አንድ ሆነን አንድ እንበል’’በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለፀ ። የቡሄ፣ ዘመን መለወጫ፣ ሻደይ፣ መስቀል፣ እሬቻ እና ሌሎችም በዓላት በመርሃ ግብሩ የተካተቱ በዓላት ናቸው ተብሏል አዲሱን አመት አንድ ሆነን አንድ እንበል በሚል መርህ ኢትዮጵያዊነትን በሚገልፁ እሴቶች ለማክበር እየተዘጋጀ መሆኑን…

በአዳማ ከተማ በተፈናቃዮችና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተወሰኑ መጠለያ ቤቶች ተቃጠሉ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) ተፈናቃዮቹ ህገወጥነትን እያስፋፉ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይከሳሉ። ተፈናቃዮች በበኩላቸው መንግስት የገባልንን ቃል ያክብር፤ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን…

“የወልቃይትን ጉዳይ ብንሸሸው፣ ብንሸፋፍነው ሊተወን አልቻለም” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተናገሩ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህን ያሉት፤ ከአማራ ክልል ምሁራን ጋር በባህር ዳር ከተማ እያደረጉት ባለው ውይይት…

“በክልላችን ባለፉት ሁለትና ሶስት ወራት ብቻ ለውጡን የማይመጥኑ አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባራት እየተከሰቱ ስለሆነ ፣ለውጡ እንዳይቀለበስ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል”ሲሉ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አሣሰቡ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በተለያዩ…

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በክብር ወደ ሀገሩ እንዲመለስ በመንግስት ጥሪ ቀረበለት። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የሪዮ ኦሎምፒክ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በስደት ከሚገኝበት የአሜሪካ ግዝት አሪዞና ከነ ቤተሰቡ ወደ ሀገሩ በክብር እንዲመለስ ጥሪ ያደረጉለት…

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በከፍተኛ ድምቀት ለመቀበል እያደረገ ባለው ዝግጅት ላይ ሕዝቡ ተባባሪ እንዲሆን አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪ አቀረበ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የንቅናቄው የአቀባበል ኮሚቴ አባላት ፦“የናፍቆት መልዕክቶቻችንን እንቀበል”በሚል ርዕስ ዛሬ በኢትዮጵያ…
በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱ ከ50 በላይ እስረኞች ዛሬ ከቂሊንጦ እስር ቤት ተፈትተዋል።

በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱ ከ50 በላይ እስረኞች ዛሬ ከቂሊንጦ እስር ቤት ተፈትተዋል። ዛሬ ከተፈቱት መካከል በእነ ገብሬ ንጉሴ እና በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር ክስ መዝገብ የተከሰሱ ይገኙበታል። በሁለቱም መዝገብ ተከስሰው ከነበሩ መካከል ግማሽ ያህሉ ከሁለት ወር በፊት የተፈቱ ሲሆን ዛሬ…

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መዩ ሙሉቄ ወረዳ የታጠቁ ኃይሎች ባለፈው ዕሁድ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት 41 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 20 ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል፡፡…

በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል ቢቢሲ አማርኛ ባለፉት ሁለት ሦስት ቀናት ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም የመንጋ ፍትህ ከህግ የበላይነት አንፃር ምን አይነት አደጋዎች እንደተጋረጡ አመላካች ነው። በምስራቅ ወለጋ ወሊጋልቴ ገጠር ቀበሌም…