የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ያውጣውን መግለጫ ተከትሎ “መግለጫው የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ ያነሳ አይደለም፣ ከዚህ በመነሳት አስራ ሁለተኛው መደበኛ ጉባዔ እንዴት እንደሚሆን ማወቅ ይቻላል” ያሉ ወገኖች ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።

ትናንት ማምሻውን 9 የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል። የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋል የሕግ አግባብነትን በተመለከተ ጥያቄዎችን አጭሯል። ለመሆኑ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሥራ ማቆም አድማ የማድረግ መብት የላቸውም?…

በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ኦፋ ቀበሌ ትናንት ማታ በግምት ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ አስራ ሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ:: የወረዳዉ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃለፊ ሻምበል አልታዬ አለሙ እንደገለጹት ከሞቱት 12 ሰዎች መካከል…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010) በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች በአካባቢው አመራሮች የሚፈጸምባቸውን የአስተዳደር በደል በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎችና የልዩ ልዩ ብሔረሰቦች ተወላጆች በሸካ ዞን አስተዳደር የሚደርስባቸውን በደል በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውመዋል። በአካባቢው የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በቅርቡ 6 ሰዎች…

በፈረንጆቹ አቆጣጠር እሁድ ሴፕቴምበር 2, 2018 ዓ.ም በሚኒሶታ ደማቅ የሆነ የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል ተካሄደ:: አዘጋጆቹ ካወጡት መግለጫ መረዳት እንደተቻለው በሚኒሶታ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል እጅግ ያማረ፣ የደመቀ፣ እጅግ የተዋጣለት ነበር::  “የሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን የሚያኮራ ታሪክ ጽፈናል:: በስታዲየሙ ውስጥ…

በኢትዮጵያ ታትሞ የሚወጣው የ እንግሊዘኛው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ባሰራጨው ዜናው ዶ/ር አብይ አህመድ በጦር መኮንኖች ሲዘረፍ ከርሟል የተባለውን ሜቴክን ከሁለት እንዲከፈል አዘዋል:: ካለ አግባብ ያለጨረታ የወሰዳቸውን ብሄራዊ ፕሮጀክቶች መዘግየት፣ በሀብት ብክነትና በሙስና ተጠያቂ ሲደረግ የቆየው ሜቴክ አሁን…

በአለም ላይ በገዳይነታቸዉ ከሚታወቁት የካንሰር አይነቶች የሴቶችን የመራቢያ ክፍል የሚያጠቃዉ የማህፀን ጫፍ ካንሰር አንዱ ነዉ። በሽታዉ በኢትዮጵያም በገዳይነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነዉ።…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010)ለረዥም ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ  ክስልጣናቸው ተነሱ። በግብጽም አዲስ አምባሳደር ተሹሟል። ከደርግ መንግስት ግዜ ጀምሮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታን ጨምሮ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት ዶክተር ተቀዳ ዓለሙን የተኳቸው አምባሳደር ታዬ…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010) የመሰረታዊ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኩባንያ/ሜቴክ/ ለሁለት እንዲከፈል ተወሰነ። ሜቴክ በወታደራዊና በንግድ ዘርፉ ለሁለት ተከፍሎ ስራውን እንዲያከናውን በተወሰነው መሰረት በመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት የተዋቀረ ቡድን ስራውን በማከናወን ላይ መሆኑ ተመልክቷል። ከፍተኛ ዘረፋ ሲፈጸምበት እንደነበር የሚገለጸው ሜቴክ ዳይሬክተሩ የነበሩትን…

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010) የሀገር መከላከያ 13 ጄኔራል መኮንኖች ከሰራዊቱ በጡረታ ተሰናበቱ። ፋይል ጄኔራል መኮንኖቹ በጡረታ የተሰናበቱት የሐገር መከላከያ ሰራዊትን በተሻለ አደረጃጀት ለማዋቀር የተጀመረውን መርሃ ግብር ተከትሎ መሆኑ ታውቋል። ከሃገር መከላከያ ሰራዊት በጡረታ ከተገለሉት መካከል ሜጄር ጄኔራል በርሃነ ነጋሽ የመከላከያ ኮንስትራክሽን…

ፖሊስ ህብረተሰቡ እንዲረጋጋ እና ህዝቡም ሆነ ጋዜጠኞች ስለ ወንጀሉ አፈጻጸም በይሆናል ከመናገር እንዲቆጠቡ ተማጽኗል።ያም ሆኖ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን መላ ምቱ እየተሰራጨ ነው። ቀኝ ጽንፈኛ ቡድኖችም ሆነ ብለው የተሳሳቱ መረጃዎችን በማቅረብ ተጨማሪ ሰልፈኞችን ለመሳብ ቅስቀሳ ያደርጋሉ።…

በትናንትናው ዕለት የታሰሩት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ዘጠኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የታሰሩት አድማ በማስተባበር ኢኮኖሚውንና የሀገሪቱን ገፅታ የሚጎዳ ተግባር ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው እንደሆነ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡