የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጅቡቲ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ባደርጉት ሰፊ ውይይት፤ ጅቡቲና ኤርትራ ከዚህ ቀደም የነበራቸው ችግር በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት መስማማታቸውን የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።…

በደቡብና በኦሮምያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች መካከል ካለፈው ሚያዝያ ወዲህ በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ሲቪሎች ለመፈናቀል መገደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር – ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል።…

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስና መሪ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ፖሊስ አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል በመሩት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ፖሊስ ኢንጂነር ስመኛው ራሳቸውን አጥፍተዋል የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።…

በአንድ አመት ከስድስት ወር ይጠናቀቃሉ ተብሎ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የወጣባቸው የስኳር ፕሮጀክቶች ከ6 አመታት በሁዋላም አልተጠናቀቁም ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቀድሞው የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ጸሃዬ እና በሜቴክ የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር…

በሃረር ከተማ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆች በፖለቲካና በኢኮኖሚ ፍትሃዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ጠየቁ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) በከተማዋ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆች ነሃሴ 25 ቀን 2010ዓም በኢሚር አብዱላሂ አዳራሽ ባካሄዱት ስብሰባ፣ የሐረር ከተማ የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጆች የአቋም መግለጫ…

በሰላም አስከባሪነት የተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች ምዝበራ እንደተፈጸመባቸው አስታወቁ። ጉዳዩንም ለጠቅላይ ሚንስትሩ እና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀዋል። ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈቃጅነት አፍሪካን በመወከል በጎረቤት አገራት ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት…

ሮበርት ሙጋቤ በህገወጥ መንገድ ከስልጣን አውርደውኛል ድምፄንም አልሰጣቸውም ያሏቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋ በምርጫ ማሸነፍን እቀበላለው ብለዋል።

አቡነ ማትያስ ዛሬ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ህዝቡ ከምንም በላይ ለፍቅር እና ቦታ እንዲሰጥ ተማጽነዋል። በሀገሪቱ የሚካሄደው ለውጥ እንዳይሰናል ህብረተሰቡ በመጪው ዓመት መቃቃር እና ጥላቻን ከሚያስከትሉ አባባሎችም እንዲርቅም ጠይቀዋል።…

የእሴት ታክስ ጭማሪው በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን የነዳጅ ምርት አቅራቢ፣ አመላላሽ እና አከፋፋይ ኩባንያዎች ሰሞኑን ሀገር ዐቀፍ የተቃውሞ አድማ መምታታቸው ደሞ ቀውሱን አባብሶታል፡፡ …