የሚጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ 2010 ዓመት በሃገሪቱ የ 27 ዓመታት ታሪክ የተለየ ስፍራ ስፍራ የሚሰጠዉ ነዉ። ከዓመታት በፊት የጀመረዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ እና አመፅ የተባባሰበት፤ ሃገሪቱ ሁለት ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የወደቀችበት፤ በሌላ በኩል በጠ/ሚ የሚመራዉ አዲስ መንግሥት አዲስ ተስፋን ያሰነቀበት ነበር።…

የንቅናቄዉን ከፍተኛ መሪዎች አስከትለዉ ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት ዶክተር ብርሐኑ ነጋ አቀባበል ላደረገላቸዉ ሕዝብ እንደነገሩት ፓርቲያቸዉ ኢትዮጵያን ለማረጋጋት እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማስረፅ በፅኑ እንደሚታገልም ገልፀዋል…

ፕሮፌሰር ብርሐኑ ነጋ “እንደ ድርጅት ግማሽ እግራችን አይደለም የገባው። ጦሩን አስገብተናል። የሚገቡ የሚቀሩ አሉ። ይገባሉ። አገር ውስጥ ሆነን በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው የመጣንው” ሲሉ ተናግረዋል።አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የለውጥ አቀንቃኝ ካሏቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ሹማምንት ጋር ንቅናቄው አብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። …