በኢትዮጵያ ለሙከራ የወጣው ድፍድፍ ነዳጅ ለኤክስፖርት የሚውል አለመሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ድፍድፍ ነዳጅ ለኤክስፖርት የሚውል አለመሆኑ ተገለጸ በኢትዮጵያ ለሙከራ የወጣው ድፍድፍ ነዳጅ ለኤክስፖርት የሚውል አለመሆኑን የመአድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ በማዕድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሰፋ ኩምሳ ድፍድፍ ነዳጁ ለኢንዱስትሪዎች በግብአትነት የሚውል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ድፍድፍ ነዳጁን…
በማሰቃያነት ሲያገለግል የነበረው የጅግጅጋ ማዕከላዊ እስር ቤት  ተዘጋ ፡፡

የሱማሌ ክልል በማሰቃያነት ሲያገለግል ነበር ያለውን የጅግጅጋ ማዕከላዊ እስር ቤት በይፋ ዘጋ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውና በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይፈጸምበት ነበር የተባለውን ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራው ማእከላዊ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት ተዘጋ ፡፡ የሶማሌ ክልል…
ለጋሞ እርቀሠላም ባህልና ባይራዎቹ (የሃገር ሽማግሌዎች) እውቅና ተሰጠ ።

የጠ/ሚኒስትሩ እውቅና ለሰላም ይበልጥ እንድንሰራ አነቃቅቶናል – የጋሞ የሃገር ሽማግሌዎች በአርባምንጩ ተቃውሞ ግጭት እንዳይሰፋ ለተጠቀምንበት ባህላዊ ክዋኔ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው እውቅና ለሠላም ይበልጥ እንድንሠራ የሚያበረታታን ነው” ሲሉ የጋሞ ባይራ ሽማግሌዎች ገለጹ።ባይራዎቹ በቡራዩ ጥቃት ዙሪያ ከአባገዳዎች ጋር ቀርቦ ለመወያየትና በጋራ መፍትሔ…

ዮሐንስ አንበርብር የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ከፍተኛ የአመራር አካል የግንባሩ ጉባዔ ነው፡፡ ጉባዔው የግንባሩ አራት የፖለቲካ ድርጅቶች በእኩል ድምፅ በሚወከሉ ጉባዔተኞች የሚዋቀር ሲሆን፣ የጉባዔ አባላት ከተወከሉበት ጉባዔ እስከሚቀጥለው ጉባዔ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በቋሚ ጉባዔተኝነት እንደሚቆዩ የግንባሩ መተዳደሪያ…

ከአፋር ወጣቶች ዱኮሂና የተሰጠ መግለጫ። 13/ መስከረም 2011 ዓ.ም ለሁለንትናዊ ለውጥ የምንታገለው በሀገራችን ፍትህ፣ እኩልነት እንዲሁም የዜጎች ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ነው። የአፋር ወጣቶች በአጠቃላይ፣ ላለፉት ጥቂት አመታት፣ በተለይ ደግሞ ባለፈው አንድ አመት ከፍተኛ ትግል ውስጥ መሆናችን ይታወቃል። በአገራችን ኢትዮጲያ…
መንግሥት ሕግና ሥርዓት በአግባቡ ሊያስከብር ባለመቻሉ በየአካባቢው ዘግናኝ ጅምላ ጭፍጨፋ መበራከቱን አብን አስታወቀ።

መንግሥት ሕግና ሥርዓት በአግባቡ ሊያስከብር ባለመቻሉ በየአካባቢው የደቦ ፍርድና ዘግናኝ ጅምላ ጭፍጨፋ መበራከታቸውን፣ በምሥረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ፡፡ አብን ይህን ያስታወቀው የመመሥረቻ ጉባዔውን በሰኔ ወር በባህር ዳር ከተማ ካካሄደ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ፣ ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2011…

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማና በአካባቢው ላይ በተፈጸመ ግድያ፣ ከባድና ቀላል የአካል ማጉደል፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት የተጠረጠሩ 312 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው የቀረቡት፡፡ ከመስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም.…