በሃገራት መካከል ያለው ትብብርና አንድነት አደጋ ላይ ወድቋል

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በሃገራት መካከል ያለው ትብብርና አንድነት አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ ገለጹ። ዋና ጸሀፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ በመካሄድ ላይ ባለው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደገለጹት ስርዓትና ደንብ ያስያዘውና ህዝቦች ተቀራርበው ለጋራ ዓላማ እንዲሰሩ ሲያደርግ የነበረው…

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ። ፍርድ ቤቱ በዋስ እንዲወጡ ትላንት ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን አቃቢ ሕግ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ እጠይቃለሁ ማለቱ ተመልክቷል። በሃገሪቱ ላይ የ70 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ኪሳራ አድርሰዋል በሚል ተጠርጥረው የአየር…

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ከተከሰተው አልመረጋጋት ጋር በተያያዘ የታሰሩት ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ። የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችና አባላት ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ወቅት አስተባባሪ በመሆን ሲሰሩ የነበሩት ሁለቱ ወጣቶች የታሰሩት በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች…
ይህ ቀን እንዲመጣ መስዋዕትነት ለከፈሉ ዜጎች እውቅና ሊሰጥ ይገባል

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011)በጨቋኙ መንግስት እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ቦታዎች ቁም ስቅላቸውን ላዩ ጋዜጠኞች ፣ የመብት ተሟጋቾች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ይህ ቀን እንዲመጣ ለከፈሉት መስዋዕትነት ታላቅ ክብር እና እውቅና እንደሚገባቸው አርቲስት እና…
የአማራ ክልል ለብአዴን ብቻ የተሰጠ ስጦታ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የአማራ ክልል ለብአዴን ብቻ የተሰጠ ስጦታ አይደለም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ። በባህርዳር ከ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ያካሄዱት አቶ ደመቀ ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተባብረን ሀገርን ማልማት ያስፈልጋል ብለዋል። ምክትል…

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በኢትዮጵያ ሕገ መንግስቱና ፌደራል ስርአቱ እየተጣሰ መሆኑን ሕዝቡ ተገንዝቧል ሲሉ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። የሕወሃት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ዛሬ የተጀመረውን የሕወሃት ጉባኤ በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ትምክህተኛው ሃይል ስርአቱን ለማፍረስና ወደ ኋላ ለመመለስ…

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የዘንድሮው የደመራና የመስቀል በአል የሚከበረው ሰይጣን ድል በተነሳበትና ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድነት በመጡበት ወቅት ነው ሲሉ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ ገለጹ። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ይህንን መልዕክት ያስተላልፉት ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረው የደመራ በአል ላይ ነው። በአዲስ…

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ የሚከበረው የደመራ በዓል በርካታ የእምነቱ ተከታዮች አደባባይ ወጥተው እንዳከበሩት DW ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል…

በአሜሪካ ኤምባሲ አዘጋጅነት ለወራት የዘለቀው አገር አቀፍ የፈጠራ ውድድር አሸናፊዎቹ ታውቀው ባለፈው ቅዳሜ ተጠናቅቋል። በውድድሩ ወጣቶች በማኅበረሰባቸው ያስተዋሉትን ችግር ለመፍታት ያስችላል ያሏቸውን የፈጠራ ሥራዎች አቅርበዋል። ለመጨረሻው ውድድር ከቀረቡ 31 ፕሮጀክቶች ውስጥ ሦስቱ ተመርጠውም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።…

ሰሞኑን ከጥቃት ያመለጡ አንድ የአካባቢዉ ነዋሪ እንዳሉት በቡድን የተሰበሰቡ ወጣቶች በተለይ ማታ በየመንገዱ ዳርቻ እያደፈጡ ወደየቤቱ የሚገባዉን ነዋሪ ያጠቃሉ፤ ይዘርፋሉም።…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሹማምንት ከዚህ ቀደም «በዋዛ የሚነኩ አልነበሩም» ያሏቸውን ጨምሮ ታጥረው የተቀመጡ 154 ቦታዎች ለመንግሥት ተመላሽ እንዲሆኑ ወስነዋል። ከ400 ሔክታር በላይ ከሚሆኑት ቦታዎች 90 በመቶው ከአጥር የዘለለ ግንባታ አልተሰራባቸውም። በሚድሮክ ኢትዮጵያ፣ በመከላከያ ሚኒስቴርና ኢትዮ-ቴሌኮም እጅ የነበሩ ይገኙበታል።…

የዓለም አቀፉ ድርጅት ጉባኤ ከጉባኤዉ በፊት እንደተጠበቀዉ ለዩናይትድ ስቴትስ እና ለኢራን መሪዎች የመወዛገቢያ መድረክ ሆኗል።የተናጥል ወይም የግለኝነት አስተሳሰብ የሚያራምዱት የዩናያትድ ስቴትስ መሪ ዶናልድ ትራምፕ  በጋራ መርሕ ከሚያምኑት ከሌሎች ሐገራት መሪዎች ትችት አላመለጡምም።…