ቴዎድሮስ ጸጋዬ መስከረም 24 2011 ዓ.ም. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የኢህአዴግን ጉባኤ ሲከፍቱ ያደረጉትን ንግግር ሰማሁ፡፡ በመልካም ቃላትና አረፍተነገሮች በጎ መንፈስ በሀገራችን ለማስፈን ያደረጉትን ሙከራ ተመልክቻለሁ፡፡ እሰየው፡፡ ነገር ግን፣ ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ጋር አናምታታ ብለው ማለትዎን አየሁና ድምጼን ላሰማ ተነሳሁ፡፡ እውነት…

በኒው ዮርክ ታላቁ ማንሃታን ክፍለ-ከተማ ከማዕከሉ ብዙም ሳይርቅ በተዘረጋው ሐርለም ቀበሌ ውስጥ 138 ዌስት 138ኛው መንገድ ላይ የቆመ ውብ የድንጋይ ጥርብ ሕንፃ ግንባታው ተጠናቅቆ የዛሬ ሥራውን ከጀመረ ዘንድሮ ልክ ዘጠና አምስት ዓመት ሞላው።
በአዲስ አበባ ሶስት የፌደራል ፖሊሶች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011)አዲስ አበባ ላይ ሶስት የፌደራል ፖሊስ አባላት መገደላቸው ተገለጸ። 5 ፖሊሶችም መቁሰላቸው ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩም የፖሊሶቹን መገደል አረጋግጠዋል። አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ሌሊት ላይ የተፈጸመውና ለፖሊሶቹ መገደል ምክንያት የሆነው ነገር…

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011) የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ አመራሮች በመንግስት የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ዛሬ ኢትዮጵያ መግባታቸው ታወቀ። በሲአን የውጭ ግንኑነት ሃላፊ በአቶ ደምቦባ ኪያናቴ የተመራው የልኡካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ሲገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተቀብለዋቸዋል። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ…

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ወደ አንድ መቶ ሺ መጠጋቱ ተገለጸ። ነዋሪዎቹን በማፈናቀልና በማጥቃት የክልሉ ፖሊስ ሃይል መሳተፉን የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ሲገልጹ የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት የክልሉ ፖሊስ በድርጊቱ አልተሳተፈም ሲሉ አስተባብለዋል። የመንግስት የአደጋ ጊዜ ሃላፊዎች…

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011)ከኢትዮጵያ የተለያዩ ስኳር ፋብሪካዎች ለስኳር ልማት ፈንድ ተብሎ የተሰበሰበው 65 ቢሊየን ብር ያህል ገንዘብ የትና ለምን አላማ እንደዋለ እንደማይታወቅ አንድ የመስኩ ባለሙያ ገለጹ። ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የፋክተሪና ሎጅስቲክ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አማረ ለገሰ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ…
የኦነግ ታጣቂዎች ትጥቅ አልፈቱም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/ ታጣቂዎች በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ትጥቅ አለመፍታታቸውን አንድ ከፍተኛ የኦነግ አመራር ገለጹ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ኦነግ በገባው ቃል መሰረት ታጣቂዎቹን ወደ ካምፕ እንዲያስገባም ጥሪ አቅርቧል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የገጠር አደረጃጀት ሃላፊና የኦዴፓ ስራ አስፈጻሚ አቶ…

የዩናይትድ ስቴትሱዋ የፊልም ኢንዱስትሪ ሆሊዉድ አድራጊ ፈጣሪ ሃርቪ ዋይንስቲን ሴት ሰራተኞቹ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ አድርሷል፡፡ ጥቃትም ፈጽሙዋል ተብሎ መወንጀሉን የዘረዘረ ሪፖርት በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ከወጣ ልክ አንድ ዓመት ሆነው።

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ( ኢሳት ዜና መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ/ም ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ በካማሺና ሌሎችም ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር በእየለቱ እየጨመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የተፈናቃዮች ቁጥር ከ150 ሺ በላይ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል። መንግስት ያቋቋመው የኢትዮጵያ…

በሰሜን ሸዋ የመብራት መጥፋት በነዋሪዎቹ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። ( ኢሳት ዜና መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ/ም ) በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች በተከታታይ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት የኤሌትሪክ መቆራረጥ በመፈጠሩ በነዋሪዎቹ እና በባለሃብቶች ሥራ ላይ ከፍጠኛ ጫና መፍጠሩን ነዋሪዎቹ…