ኢህአዴግ በሃዋሳ ሲያካሂድ የነበረውን 11ኛ ጉባዔ አጠናቀቀ ፤ ዶ/ር አብይ አህመድን እና አቶ ደመቀ መኮነንን በድጋሜ በሊቀመንበርነት እና በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል

መስከረም 25 ፤ 2011 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሃዋሳ 11ኛ ድርጂታዊ ጉባዔውን ሲያካሂድ የነበረው ኢህአዴግ ዛሬ ዶ/ር አብይ አህመድን እና አቶ ደመቀ መኮነንን እስከመጪው ጉባዔ ድረስ እንዲያገለግሉ በድጋሚ በሊቀመንበርነት እና በምክትል ሊቀመንበርነት በመምረጥ አጠናቋል ። ያስመራጭ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ…

(በመኮንን የሱፍ) መስከረም 25 2011 ዓ.ም ኢህአዴግ ያነበረው የጎሳ ፌደራሊዝም ስሁትነት ከሚገለጥባቸው ክልሎች አንዱ ከ50 በላይ የሚሆኑ ብሄሮችን አጭቆ የያዘው፣ሌሎች ክልሎች በዘራቸው ሲሰየሙ በአቅጣጫ የተሰየመው የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ነው፡፡በዚህ ክልል ውስጥ ከሚኖሩ በርካታ ብሄረሰቦች አንዱ የሲዳማ ብሄረሰብ…

ዶ/ር አብይ አህመድና አቶ ደመቀ መኮንን ኢህአዴግን እንዲመሩ በድጋሜ ተመረጡ ( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) በሃዋሳ በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ ጉባኤ ዶ/ር አብይ አህመድ ድምጽ ከሰጡ 177 ሰዎች ውስጥ የ176 ሰዎችን ድምጽ በማግኘት ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፣…

በአፍ መፍቻ ቋንቋችን እንድንማር ይፈቀድልን ያሉ የራያ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቆሙ። በአድማው 23 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) በዘንድሮ የ2011 ዓ.ም አዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታቸው መግባት የነበረባቸው የራያ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋችን…

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በድህረ ምርቃ ተማሪዎች ከፍያ ላይ 125 በመቶ የክፍያ ጭማሪ አደረገ ( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) ተማሪዎቹ ለኢሳት በላኩት መረጃ እንዳመለከቱት ዩኒቨርስቲው በድህረ ምረቃ ተማሪዎች ክፍያ ላይ 125 በመቶ ጭማሪ በማድረጉ በኑሮአቸው ላይ ጫና…

የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዎች ታወቁ ( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) ይህ ሽልማት የ25 ዓመቷን ወጣት ወ/ሮ ናዲያ ሙራድን የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማትን በወጣትነቷ ያገኘኝ ሁለተኛዋ እንስት መሆን አስችሏታል። ባለፈው ተመሳሳይ ዓመት የ17 ዓመቷ ፓኪስታኒያዊቷ ወጣት ማላላ ዩሳፊዛይ…

በየአራት ዓመቱ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት የአገራት የሰብዓዊ መብት መገማገሚያ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ለመገምገም የሚያስችል ሰነድ ቀረበ። ሰነዱን ካቀረቡት የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ፤ ሲቪከስ፣ሲፒጄ፣ዲፌንድ ዲፌንደርስ፣አርቲክል 19፣አክሰስናው፣ ፔን…

በየአራት ዓመቱ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት የአገራት የሰብዓዊ መብት መገማገሚያ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ለመገምገም የሚያስችል ሰነድ ቀረበ። ሰነዱን ካቀረቡት የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ፤ ሲቪከስ፣ሲፒጄ፣ዲፌንድ ዲፌንደርስ፣አርቲክል 19፣አክሰስናው፣ ፔን…

በኢትዮጵያ የፖለቲካ  ሂደት ብሄራዊ ምርጫ በተለያዬ ሂደትና ሁኔታ ሲደረግ የቆዬ ቢሆንም፤ ሀገሪቱ በቀጣይ ልታካሂደዉ ያሰበችዉ ምርጫ ግን ብዙወችን እያነጋገረ ነዉ። ምክንያቱ ደግሞ ሀገር ቤት ከሚገኙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጨማሪ በትጥቅ ትግል ሳይቀር ይታገሉ የነበሩ ድርጅቶች ከዉጭ ወደ ሀገር ቤት በገቡበት ወቅት…

የብሪታንያዉ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ዓመታዊ ጉባኤዉን አዘናቆአል። በበርኒግሃም በተካሄደዉ በጉባኤዉ መዝጊያ  የሀገሪቱ  ጠቅላይ ሚንስትር ተሬዛ ሜይ ባደረጉት ንግግር ሀገራቸዉ ከአዉሮፓ ህብረት አባልነቷ ከመዉጣቷ በፊት ከህብረቱ ዓባል ሀገራት ጋር ነፃ የንግድ  ስምምነት እንደሚፈልጉ አስታዉቀዋል።…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) “የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፤ የማንነት ጥያቄዎችም በህግ አግባብ እንዲፈቱ” አቋም ላይ መድረሱን አስታወቀ። ገዢው ፓርቲ ይህን ያስታወቀው ከረቡዕ መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ ም ጀምሮ በሐዋሳ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤ ሲያጠቃልል ባወጣው የአቋም መግለጫ ነው። …