ጠቅላይ ሚንስት አብይ አህመድ የካቢኔ ሹም ሽር ሊያደርጉ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በመጪው ሳምንት በፓርላማ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡና አዲስ ያዋቀሩትን ካቢኔም ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ሹም ሽሩ ያስፈለገው ሀያ ስምንት የነበሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ወደ ሀያ ዝቅ እንዲሉ በማድረግ እንዲሁም አዳዲስ…

ባለፈው ሳምንት የተካሄደው የኢህአዴግ ጉባኤ ግንባሩ ላለፉት 27 ዓመታት ሲመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚተካ ርዕዮተ ዓለም ተጠንቶ ለመጪው ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኖ ይህም በመንግስታዊ ሚዲያዎች ቢቀርብም የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ግን በ11ኛው ጉባኤ ግንባሩ የሚመራበትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም…

ትናንት ቁጥራቸው ወደ 250 የሚጠጋ ወታደሮች የመብት ጥያቄ አንስተው ወደ ቤተመንግስት ከነታጠቁት መሳሪያዎች መሄዳቸውና የተፈጸመውም ድርጊት “አደገኛ እና የመንግስት ደኅንነቱን ድከምት ያሳየ” ነበር ተባለ:: (ቢቢሲ) ቢቢሲ በስልክ ያነጋገራቸው አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ክስተቱን ‘የወታደራዊ ደኅንነቱን ድክመት ያሳየና አደገኛ’ ሲሉ ገልጸውታል።…

በአዲስ አበባና አካባቢው በስምሪት ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ከመብት እና ጥቅማጥቅም ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ማቅረባቸው መብታቸው ቢሆንም ነገር ግን ይህንን ለማድረግ በጅምላ የመጡበት ሁኔታ አግባብ እንዳልነበር ዶ/ር አብይ አህመድ እንዳስጠነቀቋቸው ተገለጸ:: ምንም እንኳ በቴሌቭዥን መስኮት…

እጅግ ተቀራራቢ የሆነ ዘረመል ያላቸው(የቅርብ አያት ካላቸው) ወገኖች በሚመሠርቱት ግንኙነት ዝርያ የሚፈጠርበት ሂደት ኢንብሪዲንግ(Inbreeding) ይባላል፡፡ በዚህ መልኩ የሚፈጠሩ ዝርያዎች ተፈጥሯዊ ጥንካሬያቸውን ማጣት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ውስብስብ ችግሮችም ይገጥሟቸዋል፡፡ ይህ የተፈጥሮ አቅም ማጣትም ቀስ በቀስ የዝርያውን የመባዛት ዕድል እየቀነሰው ይመጣና ከምድረ…

በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦነግ ጦር ሰራዊት ትጥቁን መፍታት አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ዙሪያ ሰሞኑን የተለያዩ ሃሳብና አስተያየቶች ሲሰጡ እንደነበር ይታወሳል። አንዳንዶች ከዚህ ቀደም በህወሓት/ኢህአዴግ የደረሰበት በደል፣ እንዲሁም በአንዳንድ የሀገሪቱ አከባቢዎች የጦር መሳሪያ የታጠቁ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች መኖራቸውን…
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በማንነታቸው ምክንያት ተባረዋል፤ በግፊት ስራ ለቅቀዋል፤ ተሰቃይተዋል!

ከአራት አመት በፊት ነው። ለአየር መንገድ ሰራተኞች አንድ ኢሜል ይደርሳል። የመልዕክቱ ይዘት እነ ተወልደን ይመለከታል። የአንድ ጎጥ ሰዎች በአየር መንገዱ ላይ የሚሰሩትን የሚገልፅ ነው። ለሰራተኞቹ ለደረሰው አንድ መልዕክት 24 የአየር መንገዱ ሰራተኞች “እናንተ ነው የፃፋችሁት” ተብለው ስቃያቸውን አዩ። የአየር መንገድ…

በሃዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ መስከረም 29/2011 ዓ.ም ምሽት በተለምዶ አሮጌው ገበያ ተብሎ በሚጠራው ትልቁ የከተማው የገበያ ሥፍራ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ የነጋዴዎቹን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ማውደሙን ነዋሪዎች ገለፁ።

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011)ከድሬደዋ ወደ ቢሾፍቱ ከአንድ ወር በፊት ሲበር የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አውሮፕላን የምርመራ ውጤት ይፋ ተደረገ። የኢትዮጵያ አየር ሃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት አውሮፕላን ምንም የቴክኒክ ችግር እንዳልገጠመው በምርመራ ተረጋግጧል። ነሐሴ 24/2010 ከረፋዱ 3…

ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድና ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሀገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ ጦር ከተውጣጡ የጦር ሰራዊት አባላት ጋር ትናንት ተወያይተዋል። Ethiopian Soldiers Protesting Over Pay Meet With PM

ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሰዎች ቁጥር በቀን 390 ገደማ መድረሱን የኖርዌይ የስደተኞች መርጃ ምክር ቤት አስታወቀ። ድርጅቱ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበራቸውን ከከፈቱ ጀምሮ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መጓዛቸውን አስታውቋል። …

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011)የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ሊቀመነበር አቶ ሌንጮ ለታ ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ማለቱ ተገቢ አይደለም አሉ። ወጣቱ በባዶ እጁ ታንክ ፊት በሚጋፈጥበት ጊዜ የኦነግ ሰራዊት የት ነበር ሲሉ አቶ ሌንጮ ለታ በሀገር ውስጥ ከሚሰራጨው አሀዱ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል።…