(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በሻሸመኔ ከተማ ባለፈው ነሐሴ አንድን ግለሰብ ዘቅዝቀው በመስቀል የገደሉና በዕለቱ ብጥብጥ አስነስተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ለፍርድ መቅረባቸው ተገለጸ። ነሐሴ 6 ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድን በተዘጋጀው አቀባበል ላይ ግርግርና ሁከት በመፍጠር ግለሰቡን በአሰቃቂ ሁኔታ ግድለዋል ተብለው ከተጠረጠሩት…

ዶ/ር አወል በማከል “በሕገመንግሥትና በሕግ በግልፅ እንደተቀመጠው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በሰላማዊ መንገድ ትግል ለማድረግ መርጦ ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ታጣቂዎች ሊኖሩት” አይገባም ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011)በማንነቴ በደረሰብኝ ጥቃት አየር መንገዱን ለቅቄ ወደ ግብርና ገብቼአለሁ በሚል በአማራ ቴሌቪዥን ለተናገሩት ግለሰብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ሰጠ። በዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ተወለደ ገብረማርያም ፊርማ በተሰጠ ምላሽ የአማራ ቴሌቪዥን አየር መንገዱን ይቅርታ እንዲጠይቅም ያሳስባል። ከባርነት ነጻነት ሞትን…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011)በጋምቤላ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወምና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የለውጥ እንቅስቃሴ የሚያደናቅፉ አመራሮች ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነገ በሚኒሶታ ተጠራ። የጋምቤላን ሁኔታ መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው ጫና ለመፍጠር ታስቦ በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በሚኒሶታና አካባቢዋ የሚኖሩ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በቡራዩ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው ብጥብጥ ሆቴሎቻቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የከተማው ነዋሪዎች እስካሁን ስራ ያለመጀመራቸውን አመለከቱ፡፡ ባለሆቴሎቹ ለኢሳት ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለደረሰው የንብረት ውድመት የከተማው መስተዳድር የወደመውን ንብረት ምዝገባ እና ግምት ቢያካሂድም እስካሁን ወደስራ እንዲመለሱ ለማድረግ ይህ ነው የሚባል…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011)በደቡብ አፍሪካ ለኢትዮጵያ ነጻነትና ፍትህ ድምጻቸውን በማሰማት የሚታወቁት ሼህ ወርቁ ኑሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሼህ ኑሩ ላለፉት 20 ዓመታት በደቡብ አፍሪካ በሚካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል…
የቤንሻንጉል ተፈናቃይ እናቶች በመጠለያ ውስጥ ልጆቻቸውን ተገላገሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው በኦሮሚያ ክልል ከተጠለሉ ተፈናቃዮች ውስጥ ከ20 በላይ ነፍሰ ጡር እናቶች በመጠለያ ውስጥ መገላገላቸው ታወቀ። ሌሎች 53 ወራቸው የገባ ነፍሰ ጡሮች የመውለጃ ጊዜያቸውን እየጠበቁ መሆናቸው ተመልክቷል። የነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ነፍሰ ጡሮችንና እመጫቶቹን በመንከባከብ ላይ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በሸካ ዞን ቴፒ በየኪ ወረዳ  እርምጭ ቀበሌ  ጎረፌ በሚባል  መንደር  በተፈጸመ ጥቃት ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በጥቃቱ ምክንያት ከሰባ በላይ አባዎራዎች ተፈናቅለው በቴፒ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ መጠለላቸው ተነግሯል። በሸካ አሁንም አካባቢውን ለቃችሁ ሒዱ…

ዋልያዎቹ በኬንያ የመልስ ጨዋታቸውን እሁድ በካሳራኒ ስታዲየም ከአስር ሰዓት ጀምሮ ያደርጋሉ። አሰልጣኛቸው አብርሐም መብራሕቱ ዝግጅቱን በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።…