አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ፡ የፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል የቦርድ አባል፤ ግብረ ኃይላቸው ስለምን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር  የቀድሞው የኢሕዲሪ ፕሬዚደንት ከዚምባቡዌ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የሕግ ብይን ሊሰጣቸው እንደሚገባ  እንደጠየቀ ያስረዳሉ።

በውስጥም በውጭም ብዙ ችግሮች እያጋጠሙዋቸው እንደሆነ ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ፣ እርሳቸውን በግል እንዲሁም የለውጡ ሂደት እያጋጠመው ያለውን ፈተና ዘርዝረው አቅርበዋል። ስራቸውን የሚሰሩት ህይወታቸውን…

የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ- ከድርጅቱ ሊቀመንበር ከአቶ ኦርዲን በድሪ ጋር እየተጋጩ መሆኑ ተነገረ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) ፕሬዚዳንቱ አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ከድርጅታቸው ሊቀመንበርነት መነሳታቸውን ተከትሎ የክልሉ ምክር ቤት ኃላፊነታቸውን ባለማንሳቱ ምክንያት- አዲስ ከተሾሙት…

ከአዲስ አበባ ታፍሰው ጦላይ ታስረው ከነበሩት ወጣቶች መካከል 1 ሺህ 174ቱ ተለቀቁ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) በቡራዩ ከተማ ከተፈጸመው ጭፍጨፋ እና እሱን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ከአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ወጣቶች በጅምላ ተይዘው ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ…

አሜሪካና እንግሊዝ ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ጋር በተያያዘ በሳኡዲ አረቢያ የተዘጋጀውን የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ረግጠው ወጡ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሳኡዲ አረቢያ ንጉሳውያን ቤተሰቦችን የሚተች ጽሁፎችን በዋሽንግተን ፖስት እና በተለያዩ ታላላቅ ሚዲያዎች ላይ በማውጣት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ካሾጊ…

ባለፈው ሳምንት ለደመወዝና ለጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ከነትጥቃቸው ወደ ቤተ-መንግሥት የሄዱት ወታደሮች “የለውጥ ሂደቱን የማደናቀፍ ዓላማ ባላቸው አካላት የተላኩ ነበሩ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልፀዋል።