ጉዳያችን/Gudayachn ጥቅምት 14/2011 ዓም (ኦክቶበር 24/2018 ዓም) መነሻ  የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአደገኛ መልኩ በብሔርተኝነት (በጎሳ) ፖለቲካ መናጥ የጀመረው ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ አዲስ አበባን በ1983 ዓም ከተቆጣጠረ ጀምሮ ነው።አንዳንዶች የብሔር አደረጃጀቶች ቀደም ብለው መኖራቸውን በማንሳት የኢትዮጵያን የብሔር ፖለቲከኞች ድምፅ መሰማት የጀመረው ቀደም ብሎ…

ለሐረር ከተማ ይደርስ የነበረው የውኃ አቅርቦት የሁለት ማምረቻና ማከፋፈያዎች ሥራና አቅርቦት በአካባቢዎቹ የሚገኙ ናቸው በተባሉ ሰዎች ከተስተጓጎሉ በኋላ በተደረጉ የተለያዩ ጥረቶች “በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ መፍትኄ ይገኛል” ሲሉ የሐረሪ ክልል የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አስታውቀዋል።
ሳህለወርቅ ዘውዴ በነገው እለት የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን እንደሚሾሙ ተሰማ

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴምንጭ: የተባበሩት መንግስታት ድርጂት መረጃ ማዕከል ቦርከና ጥቅምት 13 ፤ 2011 ዓ.ም. በነገው ዕለት የፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመን የመልቀቂያ ጥያቄ ለማጽደቅ የተጠራው የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ልዮ ስብሰባ (በዚህ ዓመት ሁለተኛው ልዮ ስብሰባ መሆኑ ነው) በሚለቁት ፕሬዝዳንት…

“የመዋዕለ ንዋይ ፍሰቱ እንዳይቋረጥ” ሲሉ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት አሳስበውኛል። ያ ማለት ግን፤ ጉዳዩን በሚመለከት ምንም አያደርጉም ማለት አይደለም። ለወንጀሉ ተጠያቂ የሚያደርግ .. ምንም ይሁን ምን .. የሆነ ቅጣት መኖር አለበት።

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የአየር ንብረት ለውጥና የመሳሰሉት ዓለምቀፍ ፈተናዎችን በድል ለማለፍ ያለመታከት መታገል ያስፈልጋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ጥሪ አቀረቡ፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የአየር ንብረት ለውጥና የመሳሰሉት ዓለምቀፍ ፈተናዎችን በድል ለማለፍ ያለመታከት መታገል ያስፈልጋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ጥሪ አቀረቡ፡፡
በዴር ሱልጣን በግብጽ የሃይማኖት መሪዎችና በእስራዔል ፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ

 (ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011)በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንዳይታደስ በከለከሉ የግብጽ የሃይማኖት መሪዎችና በእስራዔል ፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ። እድሳቱን ለማከናወን ወደ ቤተክርስቲያኑ ሊገቡ የነበሩ ሰራተኞችን የግብጽ ጳጳሳትና መነኮሳት ክልከላ ማድረጋቸውን ተከትሎ የእስራዔል ፖሊስ ርምጃ ወስዷል። ከአንድ ዓመት በፊት ጣሪያው የተደረመሰውን…

የራያን የማንነት ጥያቄ በማንሳታችን በደል ተፈጸመብን ይላሉ፣ የጉዳዩ አስተባባሪዎችና አንዳንድ የአላማጣ ነዋሪዎች።

የራያን የማንነት ጥያቄ በማንሳታችን በደል ተፈጸመብን ይላሉ፣ የጉዳዩ አስተባባሪዎችና አንዳንድ የአላማጣ ነዋሪዎች።
ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ነገ ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011)የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በነገው ዕለት በይፋ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ተገለጸ። ላለፉት አምስት አመታት በስልጣን ላይ የቆዩትንና የስልጣን ዘመናቸው ሊጠናቀቅ አንድ አመት ሲቀረው ስልጣን የሚለቁትን ዶክተር ሙላቱ ተሾመን የሚተካ ፕሬዝዳንት በነገው እለት እንደሚሰየምም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011)ከኦብነግ ጋር በተደረገው ስምምነት ስለመገንጠልም ሆነ ህዝበ ውሳኔ የተነሳ ነገር የለም ተባለ። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ከድር የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ባለፈው ቅዳሜ በአስመራ የተደረሰውን ስምምነት አስመልክቶ ‘’በሶማሌ ክልል ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ከመንግስት ጋር ተስማምተናል’’ ማለቱን…
የአማራ ክልል ላወጣው መግለጫ ይቅርታ ይጠይቅ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011) የትግራይ ክልላዊ መንግስት በራያ ጉዳይ የአማራ ክልል ላወጣው መግለጫ የትግራይን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ  አሳሰበ። ትላንት ማምሻውን የወጣው የትግራይ ክልል መግለጫ የአማራ ክልል መንግስት የራያ ጉዳይ በሃይል መፍታት አይቻልም በሚል ላወጣው መግለጫ ምላሽ እንደሆነም ተመልክቷል። በአማራ ክልል መንግስት…
በራያ ቆቦና ዋጃ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011) በራያ ቆቦና ዋጃ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተሰማ። ህዝቡ መንገድ በመዝጋት የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ መግታቱን የደረሰን ዜና ያመለክታል። በራያ አላማጣ አፈናውና አፈሳው ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ መሆኑንም ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጸዋል። ባለፉት አራት ቀናት ከአላማጣ፣ ከዋጃ ከጡሙጋና ከቆቦ ራያ የታፈሱ ወጣቶች ወደየት…