በአጭሩ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ በወረራ የተወሰደው መሬቱና በሃይል የተገፈፈው አማራነቱ  ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማስመለስ እንጂ በወረራ ለሰፈሩት የትግራይ ተወላጆች የሚያመችና ባለ ዕርስትነት የሚያረጋግጥ “የራስ ገዝ” አስተዳደር ለመጠየቅ የሚያበቃው ምንም አይነት ምድራዊ ምክንያት የለውም። አይኖረውም።

ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣብያ (ኢቢሲ) ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።የመጀመርያ ክፍል እነሆ: – Ethiopian opposition political organisation, founded in 2008, Patriot Ginbot 7 chairman Professor Birhanu Nega interview with state tv-EBC ጥቅምት 29/2011 ዓም   ጉዳያችን GUDAYACHN   www.gudayachn.com
የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና በአሜሪካ የሚያቀርቡ  ድርጅቶች የ“ጉድ ፉድ አዋርድስ” ለተሰኘ ሽልማት እጩ ሆኑ

በአሜሪካ በተለይ የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና የሚያቀርቡ ድርጅቶች ለሽልማት ዕጩ ሆኑ በአሜሪካ በተለይ የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና የሚያቀርቡ 25 ድርጅቶች የ“ጉድ ፉድ አዋርድስ” ለተሰኘ ሽልማት እኤአ የ2019 ዕጩ መሆን ችለዋል፡፡በየአመቱ የሚካሄደው የሽልማት ፕሮግራሙ 2019 ለዘጠነኛው ዙር ሽልማት እጩ የሆኑ ድርጅቶችን ስም ዝርዝር…
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ  ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ በጎንደር እና ባህር ዳር ከተሞች ጉብኝት ያደርጋሉ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።ፕሬዚዳንቱ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ በጎንደር እና ባህር ዳር ከተሞች ጉብኝት ያደርጋሉ።ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዓርብ ጎንደር ከተማ የሚገቡ ሲሆን፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ያደርጉላቸዋል። በቆይታቸውም በጎንደር…

በደቡብ ክልል፤ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን ወደ አዲስ አበባ የሚያቀናው መንገድ በዛሬው እለት ዝግ እንደነበር አንድ የዐይን እማኝ ለDW ተናገሩ። ሰባት ወረዳዎች ባሉት በዚህ ዞን የተለያዩ ሥፍራዎች ትናንት እና ከትናንት በስትያ ሰልፎች መካሄዳቸውን የዐይን እማኙ አክለው ገልጠዋል። ዝርዝሩን እነሆ ፦

በመተማ ግጭት ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ ዜጎች ከከተማዋ ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ገላባት መግባታቸው ታወቀ በግጭቱ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ በመተማ ከተማ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ዜጎች ከከተማዋ ተፈናቅለውል፡፡ የቅማንት ብሔረሰብ አባላትም የግጭቱ ሰለባ እንደሆኑ ተፈናቃዮች ተናግረዋል፡፡  

በዚህ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል። ሹመታቸውም በሥራ ላይ ያለውን ሕግ የሚጻረር ነው ተብሏል። ወ/ሪት ቢልለኔ ለማስተርስ ዲግሪ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሁፍ “Transformative Spaces: Enabling Authentic Female Leadership Through Self…

ሕገ-ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ለክልሉ ህዝብ አስጊ እየሆነ መምጣቱን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የመዘዋወሪያ ስልቱ እተለዋወጠ መምጣቱም ቁጥጥሩን አስቸጋሪ እደረገው መሆኑን ነው ፖሊስ የገለፀው፡፡ ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ 3 የእጅ ቦንቦች፣ 26 ሕገ-ወጥ ሽጉጦችና ከ1300 በላይ የተለያዩ ጥይቶች በቁጥጥር ስር…

መኖሪያቸውና የትውልድ ቦታቸው ወልቃይት ጠገዴ ተብሎ በሚታወቀው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሑመራና ቃፍታ ወረዳዎች የሆኑ 180 ግለሰቦች፣ ‹‹የአማራ የማንነት ጥያቄ አንስታችኋል›› ተብለው ከቀዬአቸው ተባረው አዲስ አበባ ከተማ የመጡ ቢሆንም፣ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ በፖሊስ መታገታቸው ተገልጾ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ቀረበ፡፡