ሰሞኑን በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው የመግለጫ እሰጥ አገባ ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ እንዳይቀየር ፍርሃቻ አለ። የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ወደ አማራ ክልል ለጉብኝት መምጣታቸው በህወሓት አቀንቃኞች ዘንድ በፍርሃቻ እየታየ ነው፤ ሌሎች የዘር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ጉብኝቱን ስህተት ነው…
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከሰባት ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። ወይዘሪት ብርቱካን አዲስ አበባ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ወይዘሪት ብርቱካን በመንግስት ጥሪ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን በከፍተኛ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጣቢያ ልትገነባ መሆኗን አስታወቀች። በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ምክትል ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ዋና ሃላፊ ጄነራል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በቀይባህርና ህንድ ውቅያኖስ አቅራቢያ የባህር ሃይል ሰፈር ልትገነባ በዝግጅት ላይ ናት። በአፍሪካ ትልቅና ጠንካራ…
በኦነግ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011)በኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት በመንግስት በኩል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። እየታዩ ያሉት ችግሮችም ከዚሁ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን በማመልከትም ጦርነት የሚባል ነገር አሁን የለም ሲሉም አስረድተዋል። ጄኔራል ብርሃኑ እንዳሉትም በቅርቡ ወደ ቤተመንግስት…

“ከመንገድ ተይዛ እንደ ትልቅ የጦር ምርኮኛ እየተንገላታች ነበር ወደ እስር የተወደችው። .. የዛን ጊዜ ይህንኑ ካሜራ የያዙ ጋዜጠኞች ሰለ እርሷ ወንጀል ነበር ዘገባ ለማቅቅረብ ይሯሯጡ የነበረው።” አንጋፋው የመድረክ ሰው ደበበ እሸቱ። “በመጻፍ እና ጥያቄዎች በማንሳታቸው ብቻ አንዳንዶች ለእስር ተዳርገዋል። አሁን…

“ከመንገድ ተይዛ እንደ ትልቅ የጦር ምርኮኛ እየተንገላታች ነበር ወደ እስር የተወደችው። .. የዛን ጊዜ ይህንኑ ካሜራ የያዙ ጋዜጠኞች ሰለ እርሷ ወንጀል ነበር ዘገባ ለማቅቅረብ ይሯሯጡ የነበረው።” አንጋፋው የመድረክ ሰው ደበበ እሸቱ። “በመጻፍ እና ጥያቄዎች በማንሳታቸው ብቻ አንዳንዶች ለእስር ተዳርገዋል። አሁን…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) የራያዎች ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄ የማንነት እንጂ የልማት አይደለም ሲል የራያ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል ዛሬ በአላማጣ ከተማ  በጠሩት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ የተናገሩትን ተከትሎ ለኢሳት በላከው መግለጫ እንደገለጸው ማንነቴን…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) የሀረሪ ክልልን ለ12 ዓመታት ያስተዳደሩት አቶ ሙራድ አብዱላሂ ከስልጣናቸው ተነሱ። ፋይል በምትካቸው አቶ ኦሪዲን በድሪ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው መሾማቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሀረሪ ገዢ ፓርቲ ሃብሊ ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብን ተከትሎ ከስልጣናቸው የተነሱት አቶ ሙራድ ቤተሰባዊ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011)በአፋር ዛሬ በተካሄደ ህዝባዊ ተቃውሞ ፖሊስ የሃይል ርምጃ መውሰዱ ተገለጸ። በአዳር ወረዳ ኤልውሃ በተሰኘች ከተማ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመበተን የክልሉ ልዩ ሃይል በወሰደው ርምጃ በርካታ ሰዎች በስለት ተወግተውና ተደብድበው ሆስፒታል መግባታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አንድ የሀገር ሽማግሌን ጨምሮ…