ሜቴክ ላይ ሲደረግ የነበረው ምርመራ እየተገባደደ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- መንግስት በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ውስጥ ተፈፅሟል የተባለውን ከፍተኛ ሙስና ማጣራት ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል። በማጣራቱ ሂደት በርካታ መረጃዎች ተሰብስበዋል። ይሁንና ከመስሪያ ቤቱ የተሰወሩ፣ ያልተሟሉና የተጭበረበሩ መረጃዎችን የማጣራቱ ስራ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ዋዜማ ከምርመራው ጋር ቅርበት ካላቸው ምንጮች እንደሰማቸው…

ጎንደር አጽማቸው ያረፈበት በመሆኑ ትስስራችን በደም ብቻ ሳይሆን ላልገባቸው የተሳሰርነው በብዙ ነገር መሆኑን አሳይተናል፡፡››ጠ/ሚ ዶር.ዐብይ አህመድ

(በመስከረም አበራ) ጥቅምት 3 ፤ 2011 ዓ.ም በ1983 ዓ.ም አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ህወሃት ቀጣይ ሥራ ያደረገው የትግራይን ግዛት ማስፋፋት ነበር፡፡ይህ የረዥም አመት ፕሮጀክት የተጀመረው ከጎንደር ወልቃይትን የመሰሉ፣ከወሎ ራያን የመሰሉ ለም መሬቶችን ልምላሜ ወደ ሚያጥራት ትግራይ ክልል በማካለል ነው፡፡ይህ ህወሃት በአማራው…

ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከዘይኑ ጀማል ቀደም ብሎ ለቀናት ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ሆነው ተሹመው የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ታሰሩ:: ትንናት የታሰሩት የጦር መኮንኖች ቁጥር ወደ 50 ያደገ ሲሆን ከሃገር ያመለጡ እንዳሉም ተዘግቧል:: ካፒታል የ እንግሊዘኛው ጋዜጣ ምንጮቼ…

በጎንደር ወልቃይት ተወለልዶ ያደገው ሲሳይ በአዲስ አበባ ከሚታተመው ጊዮን ከተባለው መፅሄት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የታሰረው መስከረም 11 ቀን 1986 እንደነበር አስረድቷል፡፡ መጀመሪያ በትግራይ ሽሬ ከተማ ከጓደኛው ጋር መታሰሩን የገለፀው ሲሳይ ጓደኛው ከአምስት አመት እስር በኋላ እዛው እስር ቤት መሞቱን ገልፆዋል፡፡…

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት እንዳለበት አሳሰቡ፡፡ ፕሮፌሰሩ ሲናገሩ ‹‹ይህ የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት አለበት፡፡ ደርግ 17 አመት በጠመንጃ ገዛ፣ የአንድ ትውልድ ልጆችን ገድሎ መጨረሻ ራሱም ተዋረደ፡፡ ኢህአዲግም በ27 አመታት ያንኑ ሞከረ፡፡ ህዝብን ዘላለም በጠመንጃ መግዛት አትችልም፡፡ ህዝብን የምትመራበት የተሸለ…

ዶ/ር አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒሥትርነቱን ሥልጣን ከያዙ ወዲህ በየአካባቢው የሚደረጉ በአብዛኛው ብሔርን ምክንያት ያደረጉ ግጭቶች እየተባባሱ መጥተዋል። ቀደም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች ጎላ ብለው መታየት ያልቻሉ ጥያቄዎች በአሁኑ ወቅት የብዙዎችን ሕይወት የሚያጠፉ፣ በርካታ ሀብት እና ንብረት የሚያወድሙ ግጭቶችን እያስከተሉ ነው።  

በመጀመሪያ አልበሙ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ እዮብ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ በኋላ የቀድሞ ባለቤቱና ጓደኛው ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የመጨረሻ አልበሙን የዛሬ አንድ ዓመት ለአድማጭ ጆሮ አድርሰዋል። ድምፃዊ እዮብ ሠርቶ ያገኘውን ብር ለተቸገሩ ሰጥቶ ይጨርስ እንደነበር ጓደኞቹ ይናገራሉ።…