ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኦክቶበር 31, 2018 በአውሮፓ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ጠቅላይ ሚኒስትራዊ ቀነ ቀጠሮ ይዘው ተወያይተዋል። ‘ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል’ እንዲሉ፤ ቅን ዕሳቤው ከመነሻው ፖለቲካዊ ሁከት ገጥሞታል። ሰንደቅና አርማ የሻጉራ ተያይተዋል። የብሔርና ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ለእሰጥ አገባ ደርሰዋል። ይሁንና…

በትጥቅ ትግል መቀጠል የሚፈልግ ካለ መንግሥት በሰላም አሳምኖ ለመመለስ ጥረት ማድረግ አለበት፤ ካለበለዚያ “መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ግዴታ ስላለበት በወሰነበት መንገድ ሁኔታውን መቆጣጠር ይችላል” ብለዋል የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ።

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 6/2011) በዜጎች ላይ የሰብአዊ መብት ሲፈጽሙ በነበሩ ባለስልጣናት ላይ መንግስት የጀመረውን ለፍርድ የማቅረብ ዘመቻ እንደሚደግፈው ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ገለጸ። የጥቃቱ ሰለባዎችን በተመለከተ የሰበሰባቸውን መረጃዎች ለሕግ አስከባሪ አካላት እንደሚሰጥም አስታውቋል። የፍርድ ሔደቱ ከበቀል የጸዳ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል። ከተመሰረተ ሩብ…

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 6/2011)ወንጀለኞችን እያደኑ ለፍርድ የማቅረቡ ተግባር እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ኢትዮጵያ ቢሊየን ብር የመዘበሩ በነጻነት የሚኖሩባትና አንድ ብር አጥተው ከቆሻሻ ገንዳ ምግብ የሚፈልጉ ሁለት አይነት ዜጎች ሊኖሩባት አይገባም ሲሉም አሳስበዋል። አራዊት እንኳን የማይፈጽመውን ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች…

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 6/2011) የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የ205 ግለሰቦች የባንክ ሒሳብ እንዲታገድ አደረገ። ፌደራል ፖሊስ በቀድሞ የደህንነትና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ስም የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች መረጃ እንዲሰጠው በጠየቀው ደብዳቤ በተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ሚስትና ልጆቻቸው ስም የተከፈቱትን በዝርዝር ገልጿል። በሌብነት…

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 6/2011) በሶማሊያ የኢትዮጵያ ጦር አዛዥና በኢጋድ የዋና ጸሃፊው የፖለቲካ አማካሪ ኮለኔል ገብረእግዚአብሔር አለምሰገድ በተለምዶ ገብሬ ዲላ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። በኮንትሮባንድ ንግድና በሶማሌ ክልል በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጃቸው እንዳለበት የሚጠረጠሩት ኮለኔል ገብረእግዚያብሄር ባለፈው ሳምንት በጂጂጋ ከተፈጠረው ግጭት…