በትግራይ የድብቅ እስር ቤቶች አሉ መባሉ የተለያዩ ወገኖችን እያወዛገበ ነዉ።

ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ-ሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫ «ድብቅ እስር ቤት» የሚባል እንደለሌ አስታዉቀዉ ነበር።አረና ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ የተባለዉ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ግን ትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌ ዉስጥ ቢያንስ አንድ የድብቅ እስር ቤት መኖሩን እንደሚያዉቁ ተናግረዋል። ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ መስተዳድር በተለያዩ…
ቴፒ ውጥረት ነግሷል ፤ ህዝብ ከተማውን ለቆ ጫካ ገብቷል

የቴፒ ህዝብ የድረሱልን ጥሪ እያሰማ ነው ለመረጃ ኮም በደረሰው መረጃ መሰረት በአሁኑ ሰአት ልዩ ሀይሎች ህዝቡን በመደብደብና በማሰር ላይ ናቸው የቴፒ ህዝብ ከተማውን ለቆ ጫካ ገብቷል ህይወቱን ለማትረፍ የሚመለከተው አካል ተሎ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው ይማፀናሉ።

የደብረጽዮን እና የሞንጆሪኖ ሕወሓት ለምን ጌታቸው አሰፋን አሳልፈው አይሰጡም? የሚለውን መረጃ ላቀርብላችሁ ስዘጋጅ የሕወሓቱ ሦስተኛ ሰው ጌታቸው ረዳ በኤል ሊቲቭ ላይ ወጥቶ ቃለምልልስ ሰጥቷል:: ቃለምልልሱን የተመለከተ አንድ ጋዜጠኛ ጌታቸው ረዳ “አራጁን ጌታቸው አሰፋ መናኝ እስኪመስል ዋሸን! የሚጠበቅ ነው!” ብሎታል:: ይህን…
በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ላይ በደረሰው እና እየደረሰ ባለው ጉዳት ከአብን የተሰጠ መግለጫ- አብን

***** ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ ግጭት እስከ አሁን ባለን መረጃ መሰረት የ3 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉንና ከ40 በላይ ተማሪዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው፤ ሌሎችም ተማሪዎች በስጋት ላይ ሆነው በተለያዩ የእምነት ተቋማት ተደብቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል፡፡ በተማሪዎች ላይ በደረሰው…
የትግራይ ሕዝብን የመታደግ ግዴታ የፌዴራል መንግስቱ አለበት #ግርማ_ካሳ

የዶ/ር ደብረጽዮንን መግለጫ ተመልከቼ አዘንኩኝ። ሕወሃት የለዉጡ አካል መሆን እንደማይችል፣ በሕወሃት ውስጥ ያሉ ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች በውስጠ ሕወሃት ትግል እንደተሸነፉ፣ ክልሉ በኢትዮጵያው ቢንላድን፣ ጌታቸው አሰፋ፣ በነ ስብሃት ነጋ ቁጥጥር ስር ሙሉ ለሙሉ መሆኑ ተሰማኝ። የትግራይ ህዝብ ሰቆቃና ችግር እንደሚራዘም ታየኝ።…

ወደ ሰላም የተቀላቀሉትን የኦብነግ ታጣቂዎች ሰዉ ጂግጂጋ ላይ የተቀበላቸው ከአይሮፕላን ማረፊያው አንስቶ በመንገዶች ግራና ቀኝ ተሰልፎ እንደነበረ የገለፁት ቃል አቀባዩ ሄርሞጌ በእውኑ “የሞቀና የደመቀ ነበር” ብለውታል አቀባበሉን።

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ሰራዊት ትጥቁን ፈቶ ወደ ሀገር ቤት ገባ። የኦብነግ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባት ለሶማሌ ክልል ህዝብ ታላቅ የምስራች ነው ሲል የክልሉ መንግስት አስታውቋል። ትጥቁን ፈቶ ለገባው የኦብነግ ሰራዊትም በጂጂጋ አቀባባል ተደርጎለታል። በሌላ በኩል…

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች መቀስቀሳቸው ተገለጸ። በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዩኒቨርስቲ በተነሳው ግጭት ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። 34 ሰዎችም ክፉኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በቴፒ ሳምንታት የዘለቀው ግጭት አሁንም አልበረደም። በልዩ ሃይል በርካታ ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል።…

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በነገው ዕለት የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሆነው እንደሚሾሙ ተገለጸ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ወይዘሪት ብርቱካንን የምርጫ ቦርዱ ሀላፊ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚቀርበውን ሀሳብ መነሻ በማድረግ ድምፅ ይሰጣል ተብሏል። ወይዘሪት ብርቱካን…

(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 12/2011)የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በአፋር ክልል እገነባዋለሁ በማለት የተንቀሳቀሰበት የእንፋሎት ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በሜቴክ ሳቢያ የ36 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ማስከተሉ ተገለጸ። በጄኔራል ክንፈ ዳኘው ይመራ የነበረው ሜቴክ ከኮንትራት ስምምነቱ ውጪ ከውጭ ያስገባቸው መሳሪያዎች አሮጌዎችና ያልተሟሉ በመሆናቸው ለፕሮጀክቱ መክሸፍና…