ሕወሓትን የወከሉ የምክር ቤት አባላት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ኢ ህገመንግታዊ ነው ሲሉ ተቃውመዋል

ሕወሓትን የወከሉ የምክር ቤት አባላት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ኢ ህገመንግታዊ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።
የሶስት ሰዎችን ህይወት ባጠፋ ግለሰብ ላይ የተላለፈው የሰባት ወር ብቻ የእስር ቅጣት ውሳኔ ውዝግብ አስከተለ ።

የ3 ሰዎችን ህይወት ያጠፋው ግለሰብ 7 ወራት ብቻ ስለተፈረደበት ውዝግብ አስነሳ በአዳማ ከተማ የሶስት ሰዎችን ህይወት ባጠፋ ግለሰብ ላይ የተላለፈው የሰባት ወር ብቻ የእስር ቅጣት ውሳኔ ውዝግብ አስከተለ ። የሟች እናት ወይዘሮ ኑኑ ሞጎስ ነሃሴ 8/2010 ዓ.ም ግለሰቡ ያለመንጃ ፈቃድ…
ኢትዮ ቴሌኮም በአለም አቀፍ ጥሪዎች ላይ ከ10-40 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት ከዚህ በፊት አለምአቀፍ ጥሪዎች ላይ የነበረው ታሪፍ ከ10-40 በመቶ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ በመግለጫው ከዚህ በፊት አገልግሎት ባለመስጠታቸው ተዘግተው የነበሩ 18 ሚሊዮን የሚሆኑ ሲምካርዶች ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ…
የባሕር ኃይልና የስፔስና የሳይበር ኃይሎችን ያቀፈ  የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅን ጸደቀ

ምክር ቤቱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ የ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ስብሰባውን የጀመረው ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጅንም አጽድቋል። ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ…
በሰኔ 16 ፍንዳታ የተጠረጠሩት የደሕንነት ሹም በተጨማሪ ዘረፋ ወንጀል ተከሰሱ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት፤ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል በተጠረጠሩት፣ አቶ ተስፋዬ ዑርጌ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ፈቅዷል፡፡ አቶ ተስፋዬን ሰነዶችን በማዘጋጀትና ግለሰቦችን በማስፈራራት 600 ሚሊየን ብርና 200 ሺ ዶላር ለግል ጥቅም…
የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽንን ማቋቋሚያ አዋጅ ፀደቀ

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በሕግ ይፅደቅ ወይንስ አይፅደቅ የሚለው የህዝብ እንደራሴዎች አባላትን በእጅጉ ካከራከረ በኋላ ፀድቋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ከዚህ ቀደም ለምክር ቤቱ ቀርቦ ለዝርዝር እይታ ለውጪና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ይታወሳል፡፡ ረቂቅ አዋጁ እንዲፀድቅ…
በቅርቡ የፀጥታ መዋቅሩን እናስተካክለዋለን፡፡ (ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሙሉዓለም ባሕል ማዕከል ከፀጥታ ኃይሎች፣ ሃይማኖት አባቶች እና ከባሕር ዳር ከተማ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ (አብመድ) – ‹‹በመደራጀት ችግር ለመፍጠር እየተሰራ ያለበት ጊዜ ላይ…