በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በአፍሪካ ሙስናን ለመዋጋት የሚደረገው እንቅስቃሴ ተስፋ አስቆራጭ ነው ሲል ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። በሙስና ጉዳይ ላይ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ጥናት የሚያደርገው ተቋም ይፋ እንዳደረገው የአፍሪካ ሀገራት አሁንም በሙስና ግንባር ቀደም ሆነው ቀጥለዋል። በአለም አቀፍ ደረጃ ሙስና የተንሰራፋባቸው ሃገራት በአብዛኛው…
በሱዳን ሁለተኛ ወሩን ያስቆጠረው ተቃውሞ እንዲያበቃ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በሱዳን ሁለተኛ ወሩን ያስቆጠረው ተቃውሞ እንዲያበቃ የሐገሪቱ ጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም አሳሰቡ። በሌላም በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልመሐዲ ልጅ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉች በኋላ መለቀቋ ተሰምቷል። መንግስት 30 ሰዎች እንደተገደሉ ባመነበትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ከ40…

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በእስራኤል የአንድ ኢትዮጵያ መገደልን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ግጭት አስከተለ። ከሶስት ቀናት በፊት በቴለቪቭ በእስራኤል ፖሊስ ተተኮሶበት የተገደለው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በእስራዔል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል። ለሁለት ቀናት ሲደረግ የነበረው ተቃውሞ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ወደ ግጭት መቀየሩንም ለማወቅ ተችሏል። በግጭቱ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በአላማጣ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የምከፍለው ደሞዝ የለኝም ሲል የትግራይ ክልላዊ መንግስት ማሳሰቢያ ሰጠ። የፌደራል መንግስቱ ተጨማሪ በጀት እንዲሰጠን ስለጠየቅን እስከዛው ድረስ የምከፍለሰ በጀት የለኝም ሲሉ የክልሉ መንግስት አስታውቋል። ተወላጆቹ የክልሉ መንግስት እየወሰደ ያለው ርምጃ አግባብነት የሌለውና እኛን ለማጥቃት…
የጋምቤላ ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ ሳይደረግ ቀረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በጋምቤላ ተወላጆች ዛሬ ተጠርቶ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ሳይደረግ መቅረቱ ተገለጸ። በሁለት ከተሞች ተጠርቶ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ሳይካሄድ የቀረው አልተፈቀደም በሚል ምክንያት መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰልፈኞች ገና ከመጀመራቸው በፖሊስ እንዲበተኑ መደረጉ ታውቋል። በጋምቤላ ፍቃድ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011) በቴፒ ጋብ ብሎ የነበረው ቀውስ ዳግም ማገርሸቱ ተሰማ። የሰው ህይወት የጥፋበት ግጭት ዛሬ መቀስቀሱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኮንሶ ከአስተዳደር መዋቅር ጋር የተያያዘው ውጥረትም ሰሞኑን መባባሱን ለማወቅ ተችሏል። ለውጥ አደናቃፊ የሆኑ የደቡብ ክልል አንዳንድ ባለስልጣናት አካባቢው እንዳይረጋጋ…

የኢትዮጵያ አቃብያነ ህግ በቀድሞው በሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትና በ46 ሌሎች ሰዎች ላይ ባለፈው ዓመት በክልሉ ዘር ተኮር ግጭት ቀስቅሰዋል የሚል ክስ ትናንት መስርትዋል ሲል ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በጂቡቲ ሁለት ጀልባዎች ተገልብጠው ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅትአስተወቋል።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት (IOM) ትናንት ሁለቱ ጀልባዎች ወደ የመን ጉዞ እያደረጉ ሳሉ መገልበጣቸው ከተሰማ በኋላ ተጎጂዎችን እያፈላለገ እንደሆነ አስታውቆ ነበር። ድርጅቱ እንደሚለው ከሆነ በጀልባዎቹ ላይ ተሳፍረው የነበሩት በርካቶቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ነው። የስደተኞች መርጃ ድርጅቱ ዛሬ ላይ ባወጣው መረጃ…