(ኢሳት ዲሲ–ጥር 01/2011)በሞዛምቢክ በብድር የተገኘ የሃገር ሃብትን ያጭበረበሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተከሰሱ። የሃገሪቱ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትርን ጨምሮ በአጠቃላይ 18 ያህል ሰዎች በብድር በተገኘ 2 ቢሊዮን ዶላር ላይ የማጭበርበር ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ሲከሰሱ ሁለት ዓለም አቀፍ ባንኮችም ተባባሪ ሆነው መገኘታቸውም ተመልክቷል። የሞዛምቢክ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥር1/2011)ለውጡን ለማደናቀፍ በሚሰሩ አመራሮች ተቋማቸው እየተሽመደመደ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች አመለከቱ። በደል እየደረሰብን ነው ያሉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተመራው ለውጥ የተቋሙን ዋናና ምክትል ስራ አስኪያጆች እስከማባረር ቢያበቃም በድርጅቱ ውስጥ…

እንደ ፅዋ ማኅበር ወራቱን ጠብቆ ምርጫ ማድረግ እና ተመልሶ በዘር ፖለቲካ ኋላ ቀር ዘይቤ መመላለስ ከዲሞክራሲዊ ምርጫ ትርጉም ጋር የማይዛመድ ልማዳችን ነው፡፡ ይህ ልማዳችን የፖለቲካችንን ጉልበት ለዝለት ዳርጎ እንዳንራመድ ሲያንፏቅቀን የኖረ ክፉ ቁራኛችን ሆኖ አለ፡፡

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 01/2011) የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎችና የሰራዊቱ አባላት ከትግራይ እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉ ተገቢ አይደለም ሲሉ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። በማንኛውም መልኩ ግጭትና ጦርነት የሚቀሰቅስን ተግባር አንቀበልም ያሉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የህዝቡን ስጋት ብንረዳም የጦር መሳሪያዎቹ የፌደራሉ መንግስት ንብረት በመሆናቸው…

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2011) የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በምዕራብ ኢትዮጵያ ሕግና ስርአትን ለማስከበር በጀመረው ርምጃ 171 ግለሰቦች እንዲሁም የጦር መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ትጥቅ የማስፈታቱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የኦሮሞ…

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2011) በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በኮኪትና ገንዳ ውሃ ከተሞች በመከላከያ ሰራዊት በተወሰደ ርምጃ 8 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ትላንት ገንዳውሃና ኮኪት በተባሉ አካባቢዎች ለተቃውሞ በወጡ ነዋሪዎችና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል በተፈጠረ ግጭት ስምንት ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የሱር ኮንስትራክሽን ተሽከርካሪዎች…

(በመስከረም አበራ) ጥር 1 2011 ዓ ም ሃገራችን ለፖለቲካ ህመመሟ ፈውስ በምታገኝበት ወይም ጨርሳ የአልጋ ቁራኛ በምትሆንበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡ዋነኛ ህመሟ የዘር ፖለቲካ አመጣሽ ደዌ ነው፡፡የዘር ፖለቲካ በደም ሥሯ ገብቶ መላ አካሏን የሚያናውጣት ይህች ደሃ ሃገር ሲባል የሰማችው…

በኢትዮጵያ ስለ ሕገ መንግሥት፤ ስለ ነፃ ፍርድቤት፤ ስለ ሕግ በላይነት፤ ስለ ነፃ ምርጫ ቦርድ፤ ስለ ሕዝብ የመምረጥና የመመረጥ መብት፤ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች፤ ስለ ክልል መንግሥት፤ ስለ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ለመገንባት  ለውይይት የቀረበ ልዩ መርሐ ግብር።

በኤርትራ ድንበር አካባቢ የነበረን የኢትዮጵያ ሠራዊት ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር እየተሰራ ያለውን ሥራ ለማደናቀፍ ሙከራ እያደረገ ያለ ኃይል መኖሩን ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡

ሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ በማልታ ደሴት አቅራቢያ በሁለት የጀርመን ጀልባዎች ላይ ማረፊያ አጥተው የቆዩ አርባ ዘጠኝ ፍልሰተኞችን እንደሚያስተናግዱ የደሴቲቱ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆዜፍ ማስካት ዛሬ አስታወቁ።