ኮለኔል ጌታሁን ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ ኮለኔል ጌታሁን ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀብራቸው ስነስርዓት በዩጋንዳ በብሄራዊ ጀግና የክብር ስነስርዓት እንደሚፈጸም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ አየር ሃይል የሀገሪቱን ከፍተኛ የጀግንነት የክብር ኒሻን ካገኙት ጥቂት ሰዎች አንዱ የሆኑት ኮለኔል ጌታሁን ካሳ…

በመቀሌ ከተማ ኲሓ ክፍለከተማ ኲሓ በትናንትናው ዕለት በነበረው የፅዳት ዘመቻ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በአባላቶቼና በሌሎች ወጣቶች አካላዊ ጥቃት ተፈፅምዋል እንዲሁም ታሰሩ ሲል የዓረና ትግራይ ፓርቲ ከሰሰ።

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)ከ30 በላይ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጌዲዮ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ። አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጥሪ አቅርበዋል። ድምጻውያን፣የቲያትር ባለሙያዎች፣ ደራሲያንንና ሌሎች የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ያሳተፈው የልኡካን ቡድን አባላት ዜጎች ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል። የተፈናቀሉት ዜጎች ወደነበሩበት…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011) የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ጥረት አመርቂ አይደለም ተባለ። በሔሊኮፕተር የሚደረገው ጥረትም በቂ አይደለም ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ገልጸዋል። ውሃ በቅርበት አለመኖሩ በሄሊኮፕተር ጭምር እየተካሄደ ያለውን የማጥፋት ስራ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተመልክቷል።…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)ካምፕ የገባው የኦነግ ጦር ተመርዟል መባሉን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል የወሊሶ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች የተቃውሞ አድማ እያደረጉ ነው። በአድማው ምክንያት ከወሊሶ ወደ አዲስ አበባ፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ወደ ወሊሶ የሕዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዳይገቡና እንዳይወጡ ወጣቶች መንገድ ዘግተዋል ተብሏል።…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011) በኮማንድ ፓስት ስር በሚገኙት የሰሜን ሸዋና የኦሮሞ አስተዳደር ዞን የጦር መሳሪያ ዝውውር ገደብ መጣሉ ተገለጸ። ሕገ ወጥ የጦር የመሣሪያ ዝውውር በቅርቡ ለተከሰቱት የፀጥታ ችግሮች መንስኤ ናቸው ያለው ኮማንድ ፖስት  ከፌደራልና ከክልል ጸጥታ ሃይሎች ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ…
የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በከፍተኛ ስጋትና ውጥረት ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ/2011)የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በከፍተኛ ስጋትና ውጥረት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ ተጀመረ፡፡ የምክር ቤቱ አባላት ወደ ስብሰባው ሲገቡ ስልክ ይዞ መግባት ከመከልከሉ ሌላ ከፍተኛ ፍተሻ መደረጉ ታውቋል። ምክር ቤቱ ያለፉትን ወራት የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ…
በቤተ ክርስቲያን ላይ የቀጠለውን ጥቃት በጥናትና በቅንጅት የሚመክት የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አደረጃጀት በየከባቢው እንዲጠናከር የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት ጥሪ አቀረበ

ሥልጣንን፣ ፖለቲካን፣ ቋንቋንና ወቅትን ተገን ያደረገ ጥቃትና ትንኮሳ ዛሬም ቀጥሏል፤ የጎሠኝነትና አክራሪነት ግጭቶች፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በተለየ መንገድ ጎድተዋል፤ ከሌሎች አብያተ እምነት ይልቅ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያነጣጠሩ ናቸው፤ ግጭት በተነሣ ቁጥር የበቀል እና የጥላቻ መወጣጫ የምትደረገው ቤተ ክርስቲያን ናት፤ ለለውጡ ጊዜ በመስጠት ትዕግሥት ብናደርግም፣ግድያና ጥፋቱ በጠራራ ፀሐይ…

ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከፍተኛ አማካሪ እንዲሁም ልጃቸው ኢቫንካ ትረምፕ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከፍተኛ አማካሪ እንዲሁም ልጃቸው ኢቫንካ ትረምፕ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ በሚገኘው ጥንታዊው የኖተርዳም ካቴድራል ህንጻ ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ። የእሳት አደጋው ምክንያት እስካሁን ባይታወቅም ለህንጻው እየተደረገ ካለው እድሳት ጋር ሳይያያዝ አይቀርም ተብሏል። በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይም…