(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 9/2011)አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አቶ ለማ መገርሳ የውጭ ጉዳይና የሀገር መከላከያ ሚኒስትሮች ሆነው ተሾሙ። የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ደግሞ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ሆነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2011) በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ መፍትሄ ካልተሰጠ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ በአካባቢው የተሰማሩ የህክምና ባለሙያዎች ገለጹ። ከህክምና ቡድኑ አባላት አንዱ ለኢሳት እንደገለጹት በአካባቢው ካለው የምግብና የውሃ እጥረት ጋር ተያይዞ በርካታ ተፈናቃዮች ለከፋ አደጋ ተጋልጠዋል። ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2011)በአፋር ክልል ወጣቶችን የማዋከብና የማስፈራራት ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ። የአፋር የሰብአዊ መብት ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ከሆነ ወጣቶቹ በክልሉ ያሉት አሰራሮች ይቀየሩ በሚል በሰላማዊ መንገድ ለሚያቀርቡት ጥያቄ እየተሰጣቸው ያለው ምላሽ መሳደድ ሆኗል።…

በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በካቢኔያቸው ላይ ያደረጉትን ሹም ሽር ፓርላማው አፅድቋል። ምክር ቤቱም ሹመታቸውን በአንድ ተቃውሞ፣ በአምስት ድምፀ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። የዚህ ሹም ሽር አንድምታው ምንድን ነው?…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር በግል ህክምና ኮሌጆች የሚመረቁ ዶክተሮችን መቅጠር ማቆሙ ቅሬታ አስነስቷል። ቅሬታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡ ዶክተሮች ከአራት ወራት በላይ ሳይቀጠሩ መቆየታቸውንና ለመመረቅ የተግባር ስልጠና የሚቀራቸው የህክምና ባለሙያዎችም ወደ ተግባር ልምምድ መግባት አለመቻላቸውን ተናግረዋል።…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጀነራል ዋቆ ጉቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ዛሬ ከሰዓት በትምህርት ቤቱ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ 37…