አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብን በነጻ ከመግለጫ መድረክነታቸው ባለፈ በማህረሰቡ ውስጥ የዴሞክራሲ እሴቶች እንዲያብቡ፣  በመንግስት ዘንድ ግልፀኝነት እንዲሰፍን እና በፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር በማድረጉ ረገድ  ሚናቸው  ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር…
33 ግለሰቦች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ግጭቱን በማነሳሳትና በማባባስ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፍርድ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። በዚህ መሰረትም ግጭቱን በማነሳሳትና በማባባስ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ቁጥርም 33 መድረሱን ኮሚሽኑ አመላክቷል። ከተጠርጣሪዎች መካከልም…

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቃል-አቀባይ አቶ ገለታ ሀይሉ ጋር ዛሬ ያደረግኩት አጭር የስልክ ቃለ- መጠይቅ: Elias Meseret Taye ጥያቄ: ከቀናት በፊት በክልላችሁ በሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ አሁን ተወሰደ ስለተባለው የአፀፋ እርምጃ መረጃ አለዎት? መልስ: መረጃው ትክክል ነው።…
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ስነስርዓታቸው የፊታችን ዕሁድ ይፈጸማል

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011)ባለፈው ቅዳሜ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የፊታችን ዕሁድ የቀብር ስነስርዓታቸው እንደሚፈጸም ተገለጸ። አስክሬናቸው ቅዳሜ ሚያዚያ 26 ከጀርመን ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባም መንግስት አስታውቋል። በብሔራዊ ደረጃ የሚፈጸመው የቀብር ስነስርዓት ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝግጅት በማድረግ…
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 የዩኔስኮ ተሸላሚ ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2011)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 የዩኔስኮ የሰላም ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደረስ ባደረጉት አስተዋጽኦ ለሽልማት መብቃታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ይፋ አድርጓል። በቀድሞ የአይቬሪኮስት ፕሬዝዳንት ፌሊኒክስ ሃፌፍ-…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011)የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የትላንቱ ጉባዔ የኢትዮጵያ የእስልምና ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው ሲል አስታወቀ። በትላንቱ ጉባዔ ድል ኮሚቴው ምስጋናውን ለመላ የኢትዮጵያ ህዝብ አቅርቧል። የኮሚቴው አባል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ለኢሳት እንደገለጹት የኢትዮጵያ ሙስሊም ለዓመታት ሲጠይቅ…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2011) በአፋር ክልል ዛሬ በተለያዩ ወረዳዎች የተካሄደው ሰልፍ ለክልሉም ሆነ ለፌደራል መንግስቱ ማስጠንቀቂያ በመስጠት መጠናቀቁ ተገለጸ። በተደጋጋሚ በክልሉ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት እንዲቆም በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢኣይቀርቡም ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ ሰልፈኞቹ ይናገራሉ። ከውጭ የሚገቡ ሃይሎች የሃገርን ሉአላዊነት…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2011)በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች አዴፓንና የለውጡን አስተዳደር በመቃወም  ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ። በተለያዩ ከተሞች  የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል፡፡ የሰልፉ ትኩረት በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የአማራ መፈናቀል እና ሞት ይቁም የሚል ነው ተብሏል። የአማራ ክልል ርእሰ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዳንጉር ወረዳ በተከሰተው ግጭት ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 33 ደርሷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፍርድ…
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ አስከሬን ቅዳሜ ማለዳ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ የቀብር ስነ ስርአት ክንውን ብሄራዊ ኮሚቴ አስታወቀ።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ አስከሬን ቅዳሜ ማለዳ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል – አስተባባሪ ኮሚቴው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ አስከሬን ቅዳሜ ማለዳ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ የቀብር ስነ ስርአት ክንውን ብሄራዊ ኮሚቴ አስታወቀ። በአስከሬኑ የአቀባበል ስነ ስርአት ላይ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ወዳጅ ዘመዶቻቸው…