ስለ ደዳብ የስደተኞች መጠለያ ቀበሌ ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ከኬንያ መንግሥት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር – ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር አስታውቋል።
የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ስጋትን የሚገልጽ የድምጽ ቅጂ ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011) ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ የተለያዩ የአሜሪካን አየር መንገዶች ውስጥ የሚሰሩ አብራሪዎች ስጋታቸውን የገለጹበት የድምጽ ቅጂ ይፋ ሆነ። በሌላ በኩል የትራምፕ አስተዳደር የአቪዬሽን ባለስልጣናት ችግሩ የቦይንግ ሳይሆን የአብራሪዎቹ በቂ ስልጠና አለማግኘት ነው የሚል መከራከሪያ ይዘው…

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011) ለቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ መጥሪያ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤት በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ። ለዛሬ እንዲቀርቡ የተላለፈው የመጀመሪያው ትዕዛዝ ተፈጻሚ ያልሆነው መጥሪያው ከፍርድ ቤት ወጪ ሳይደረግ በመቅረቱ መሆኑን በዛሬው ችሎት ላይ ተገልጿል። የዋስትና…

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011)ከትላንት ጀምሮ ስራ ያቆሙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተለማማጅ ሀኪሞችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በአስተዳደር በኩል ዛቻና ማስፈራራት እየተደረገብን ነው ሲሉ ገለጹ። ፋይል ጥያቄአችንን የጥቅም ብቻ በማስመሰል የሚዲያ ዘመቻ እንዲከፈትብን ተደርጓል ሲሉ ዛሬ መግለጫ ሰተዋል። በተቃውሞአቸውም እንደሚቀጥሉ ነው ያስታወቁት። በአዲስ…

በዩናይትድ ስቴትስና በሌሎችም አከባቢዎች ከሚገኙ የንግድ ተቋማትና በ$100 ሚልዮን የሚገመት ገንዘብ ለመስረቅ የሚያስልችል የሶፍተ ዌር ፕሮግራም የሚጠቀም ዋናው መሰረቱ ምሥራቅ አውሮፓ የሆነው የሳይበር የወንጀል መረብ እንደተበተነ ታውቋል።

የየመን መንግሥትን የሚደግፈው በሳዑዲ ዓረብያ የሚመራው የጥምረት ኃይል ዛሬ ሰንዓ ላይ ተከትታይ የአየር ድብደባዎች ማካሄዱ ታውቋል። ቢያንስ ሥድስት ሰዎች እንደተገደሉ ተዘግቧል።
ጌታቸው አሰፋ በድጋሚ መጥሪያ ደርሷቸው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት  ትዕዛዝ ሰጠ

ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በሌሉበት ጉዳያቸው እየታየ ያሉ አራት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መጥሪያ ደርሷቸው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ የፌዴራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በድጋሚ ትዕዛዝ የሰጠው ሚያዚያ 30 በተሰጠው ትዕዛዝ መጥርያው ከፍርድ…
ኢህአዴግ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ  (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች…
የህዝብ ተወካዮች የሁለት ኮሚሽኖች አመራሮችን ሹመት አጸደቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2011)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁለት ኮሚሽኖችን አመራሮች ሹመት አጸደቀ። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቅራቢነት ለአመራሮቻቸው ሹመት የጸደቀላቸው ኮሚሽኖች የእርቅና ሰላም ኮሚሽንና የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ኮሚሽን ናቸው። ካርዲናል ብርሃነየሱስና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ የእርቅና ሰላም ኮሚሽን ኮሚሽነርና ምክትል ኮሚሽነር ሆነው…

ካርቱም ውስጥ ትላንት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተካሄደ ግጭት ቢያንስ ሥምንት ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ የሱዳን ገዢ ወታደራዊ ካውንስል ከሲቪል የተቃውሞ መሪዎች ጋር ሲያካሄድ የቆየውን ንግግር አቋርጧል።

የግለሰብ መብት ካልተከበረ የማንም መብት ሊከበር አይችልም ፡፡ (ምንሊክ ሳልሳዊ) ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር…
‹‹ሰልፍ ወጣን፤ ጥይት መተኮስ ጀመረ›› የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

አብመድ ያነጋገራቸው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ ችግሩ የተፈጠረው ለአንድ ሳምንት ያክል የንጹሕ መጠጥ ውኃ ባለማግኘታቸዉና ዩኒቨርሲቲው አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ የሚመለከተውን አካል ለመጠየቅ ሰልፍ በወጡበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሰልፍ ወጣን፤ ጥይት መተኮስ ጀመረ›› ብለዋል፡፡ ‹‹እኛ ሰልፍ እንደወጣን ውኃው ተለቀቀ፤ ይህ ማለት ችግሩ…