“የማይሰበረው” የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ሰኞ በገበያ ላይ ይውላል በአዳዲስ የቢዝነስና የስራ ፈጠራ ሃሳቦች አፍላቂነታቸውና በፈር-ቀዳጅ ኢንቬስተርነታቸው በሚታወቁት ኢትዮጵያዊው ኢኮኖሚስትና ባለሃብት በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ የሕይወት ታሪክና ስራዎች ዙሪያ የሚያጠነጥነውና በደራሲና ጋዜጠኛ አንተነህ ይግዛው የተጻፈው “የማይሰበረው – ኤርሚያስ አመልጋ” የተሰኘው የሕይወት ታሪክ…

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ አባላቶቻቸው አለአግባብ እየታሠሩባቸው መሆኑን ተናገሩ። የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ በበኩሉ በሕግ ጥሰት እንጂ በፖለቲካ እንቅስቃሴ የታሰረ ሰው የለም ብለዋል።

ለሕዝብ ሲደርስ የነበረው መረጃ ፍጥነት የጎደለው እና ለውዥንብር የዳረገ ነበር ሲሉ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ምሁር ገለጹ፡፡ (አብመድ) ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባሕር ዳር በከፍተኛ መሪዎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ ለሕዝብ ሲደርስ የነበረው መረጃ ፍጥነት…
የሲዳማ ክልል ጥያቄን አስመልክቶ ከየትኛውም አካል የሚሰጥ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ ምንም አይነት ተቀባይነት አይኖረውም – ኤጄቶ

DW : የፊታችን ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓም የሲዳማ ሕዝብ ደቡብ ከሚባል ድሪቶ ውስጥ ለማደር የማይገደድበት እና በራሱ ዕጣ ፈንታ ላይ በራሱ ምክር ቤት ራሱ ብቻ የወሰነበትን ውሳኔ የሚያጸናበት ቀን ነው ሲል ኤጄቶ የተባለው የሲዳማ የመብት አቀንቃኝ ቡደን አስታወቀ። ቡድኑ…

ከሰሞኑ የባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞ በየክልሉ ያሉ የ”ልዩ ኃይሎች” ጉዳይ እያጠያየቀ ነው።መንግስታዊው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ “ክልሎች ከአስር ሺዎች እስከ መቶ ሺዎች የሚቆጠር ልዩ ሃይል እንዳላቸው የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ” ብሏል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ በክልላቸው “ልዩ ኃይል የሚባል…

ብርጋድየር ጀነራል ተስፋዬ ኃብተማርያም በላቀ የጦር ሜዳ ጀግንነት የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የመጨረሻው ደረጃ የጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ናቸው፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ስፔሻል ፎርስ /ልዩ ሀይል/ በሀገር ደረጃ ከነበሩት ጥቂት የመጨረሻውን ስልጠና በሀገር ውስጥና በውጭ በእስራኤልና በአሜሪካን ሀገር ከወሰዱት ምርጥ መኮንኖች አንዱ ናቸው፡፡ ጀነራሉ…