የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፅ/ቤት ኃላፊ ታሰሩ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ በለጠ ካሳ መታሰራቸውን ምንጮች ገልፀዋል። አቶ በለጠ ካሳ ከአብን አባላትና አመራሮች ጋር ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ መኪና ውስጥ በነበሩበት ወቅት ፖሊሶች ከመኪና አስወርደው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን (3ኛ) እንደወሰዷቸው ተገልፆአል።   የአብን አመራሮችና…

Alert – የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላሉ ዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያ መልእክት አስተላለፈ። ምንም እንኳን አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ጣቢያዎች የታገዱ ቢሆንም አዲስ አበባ መደበኛ የድምፅ እና የመረጃ አገልግሎቶች አሏት ፡፡ የድምፅ ፣ ኤስኤምኤስ እና DSL አገልግሎቶች በአጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ይገኛሉ ፣ ግን…
የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የምርመራ ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል

በአማራ ክልል በሰኔ 15 ዓ.ም ተሞክሮ የከሸፈውና የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች ለህልፈት የዳረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የምርመራ ውጤት በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን እያካሄደ ባለው 5ኛ ዙር፤ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ…

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የንቅናቄ መድረክ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የሶስት ሚሊየን ችግኝ ተከላ ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስተዳደሩ መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡ በዛሬው ዕለትም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት የአረንጓዴ…

ኢትዮጵያና አሜሪካ በምስራቅ ኢትዮጵያ ሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ጥምር ወታደራዊ ልምምድ እያካሄዱ መሆናቸው ተገለፀ፡፡ ልምምዱ ለ16 ቀናት የሚቆዬውና ወታደራዊ ህክምናን ያካተተው የሁለቱ ሃገራት ጥምር ልምምድ አካል ነው ተብሏል፡፡ ዓላማውም በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦርን/ አሚሶምን ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡

VOA : በሶማሌ ክልል ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ ተፈናቅለው በባሌ ዞን የሰፍሩ ስዎች ወደ ቄያቸው መመለስ ቢፈልጉም አለመቻላቸው ገለፁ።የባሌ ዞን አደጋ መከላከል ፅህፈት ቤት እንደ ገለፀው በዞኑ ከመቶ ሀያ ሺ በላይ ተፈናቃዩች መስፍራቸውን ገልጦ ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን መንገድ ለማመቻቸት…
አቃቤ ሕግ ሰነዶቹን ሳይተረጉም ያቀረበዉ «ሆን ብሎ» ክሱ የሚታይበትን ጊዜ ለማራዘም ነዉ – አቶ በረከት ስምዖን

DW : በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን የአቶ በረከት ስምዖን፤ የአቶ ታደሰ ካሳን እና በአባሪ ተባባሪነት የተጠረጠሩትን የቀድሞ የብአዴን-ኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጉዳይ የሚዳኘዉ ፍርድ ቤት፣ አቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ ያቀረባቸዉን የሰነድ ማስረጃዎች በአማርኛ ቋንቋ ተርጎሞ እንዲያቀርብ አዘዘ። ዛሬ ባሕርዳር ያስቻለዉ የአማራ ክልል…
በጀርመን ስብሰባዎች ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሙከራዎች  ሕገ ወጥ እና በጀርመን ሕግም የሚያስጠይቁ ናቸው ተባለ

DW : የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት የተባለው ስብስብ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ኤርሚያስ ለገሠ የሚገኙባቸውን እነዚህኑ መድረኮች «የተደራጁ ኃይሎች»ያሏቸው እንደሚረብሹ ለአዘጋጆቹ ማስጠንቀቂያዎች ልከዋል።የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሠራተኞች ሲሉ የገለጹዋቸው በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች «የባልደራስ አባላት መድረክ ሊሰጣቸው አይገባም በማለት ጽፈዋል»ሲሉም ወቅሰዋል። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/CBAA3CC3_2_dwdownload.mp3 ጀርመን የሚኖሩ…

DW : ተቃዋሚውን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድን ጨምሮ ግንባር ለመፍጠር በሂደት ላይ ያሉ 7 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ መግለጫ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሰጥተዋል። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ከሰኔ 15፣2011 ዱ ግድያ በኋላ እየተፈጸመ ነው ያሉት የጅምላ እሥራት…