ወጣት ጂኔኑስ ፈቃዱ ፋርማሲስትና የወለጋ ዩኒቨርሲቲ መምሕር ነው:: ከሚያገኘው ደመወዝና ጓደኞቹን በማስተባበር ድጋፍ የሌላቸውን 20 የኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በገንዘብና የትምህርት ቁሳ ቁስ በማሟላት እንደሚያስተምር ይናገራል::

ፈቲያ መሃመድ ትባላለች፥ ተወልዳ ያደገችው ድሬዳዋ ነው። ሞዴሊስት ነች። በግንቦት 2019 አሜሪካ ላይ በተካሄደ የዓለም የማኅበረሰብ አገልግሎት ወይዘሮ ዓለም አሸናፊ ነች። ይህንን ድሏን ተጠቅማ የአካባቢዋን ማኅበረሰብ ለማገልገል ወጤታማ እንቅስቃሴ አካሂዳለች።

ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘው ወደ አራት ሚሊየን ዓመት የሚጠጋ ዕድሜ ያለው የሰው መሰልና የጦጣ መሰል ድብልቅ የሆኑ መገለጫዎች ይሉት ቅሪተ-አካል የዛሬ አርባ አምስት ዓመት አፋር ውስጥ የተገኘችው የሉሲ ወይም አውስትራሎፔቲከስ አፋሬንሲስ ቀጥተኛ ቅድመ-ትውልድ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የዩሮፓ ሊግ ሙሉ ድልድል:: ምድብ 1፡- ሴቪያ፣ አፖኤል ኒኮሲያ ፣ ካራባግ ፣ ዱደላንዥ ምድብ 2፡- ዳይናሞ ኪዬቭ፣ ኤፍ ሲ ኮፐንሃገን፣ ማልሞ፣ ሉጋኖ በምድብ 3፡- ባዜል፣ ክራስኖዳር፣ ሄታፌ፣ ትራብዞንስፖር ምድብ 4 ፡- ስፓርቲንግ ሊዝበን፣ ፒኤስቪ…

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብርሀን ለሁለም መርሀ ግብር በ12 ከተሞች እየተከናወነ የሚገኘው የአነስተኛ ሀይል ሙከራ ማመንጨ ስራ ከ3 ወር በኋላ እንደሚጠናቀቅ የውሃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች የብርሃን ለሁሉም መርሃ ግብር ዙሪያ…

በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ ፍልሰተኞች ተይዘው በሚቆዩባቸው ማዕከሎች ውስጥ በእንግሊዝኛ ስሙ “መምፕስ” በሚባል ቫይረስ ወደዘጠኝ መቶ የሚሆኑ ሰዎች መታመማቸው ተረጋገጠ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውቅያኖስ ማዕበል ተከታታይ ብሄራዊ ማዕከል ዛሬ እንዳስታወቀው፣ “ኸሪኬን ዶሪያን” ተብሎ የተጠራው የውቅያኖስ ማዕበል ዛሬ ወደኋላ ላይ እንደሚጠናከር ተናገረ።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ጥራቱ በየነ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡ አቶ ጥራቱ የተሾሙት የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ነው። ምንጭ፡- ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት