አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ1945 በጃፓን ሂሮሺማ ከተማ ከአቶሚክ ቦምብ  ፍንዳታ ከተረፉት ህንፃዎች ሊፈርሱ መሆኑ ተገለፀ። በጃፓኗ ሂሮሺማ  ከተማ በአውሮፓውያኑ በ1945 በአቶሚክ ቦምብ ፍንዳታ ወቅት ከተረፉት ህንጻዎች መካከል  ሁለት ህንፃዎችን ለማፍረስ የታቀደ  መሆኑ ነው የተነገረው። አንዳንድ  የአከባቢው ነዋሪዎች …

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 6፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም በነገው ዕለት ይጀመራል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአጭር፣ በመካከለኛ ርቀት፣ በ3 ሺህ ሜ.መሰናክል፣ በእርምጃና በሜዳ ተግባራት ከታህሳስ 7 እስከ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበበ ስታዲየም ነው የሚካሄደው፡፡ በመክፈቻው እለትም የአሎሎ…

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው። የውይይት መድረኩ በሁለቱም ክልሎች ባሉ ዩኒቨርስቲዎችበሚከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ በመምከር የመፍትሄ ሃሳብ ለመጠቆም ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ባለፈም ውይይቱ በሁለቱ ክልሎች ህዝቦች መካከል…

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 6፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን በፈረንጆቹ እስከ የካቲት ወር 2020 ድረስ ለማራዘም ተስማምተዋል። የደቡብ ሱዳን መንግስት እና በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በትናንትናው ዕለት በዋና ከተማዋ ጁባ ተወያይተዋል። በምክክር መድረኩ በደቡብ ሱዳን ሉዓላዊ ምክር…

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ ከሰሞኑ ያወጣቸው አዲሱ የዜግነት ህግ ተቃውሞ እንደገጠመው ተነግሯል። በዋና ከተማዋን ዴልሂ ጨምሮ በሰሜን እና በምስራቅ ሕንድ ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን፥ ተቃዋሚዎችም አውቶቡሶችን እያቃጠሉና መንገዶቹ እየተዘጉ ነው ተብሏል። ፖሊሶችም በዋና ከተማዋ ዴልሂ  ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ…

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የመንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዓለም አቀፉ የስደተኞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ስዊዘርላንድ አቅንቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጄኔቫ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን…

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ) ትኩረቱን በስደተኞች ላይ ያደረገው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ፎረም በጄኔቫ ይካሄዳል። ፎረሙ ለሶስት ቀናት በስደተኞችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። ትምህርት፣ የስራ እድል ፈጠራና የዜጎች የገቢ ምንጭ፣ ሃይልና…

ክራይስስ ግሩፕ እንደሚለው ከሆነ ምርጫው በተያዘለት ጊዜ የሚካሄድ ከሆነ ቀደም ብሎ ቁልፍ ተቃዋሚ ኃይሎችንና ሲቪል ማህበራትን በማሳተፍ ከምርጫው በፊትና በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን ለማስወገድ ተከታታይ ውይይቶችን ማድረግ ያስፈልጋል።…

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሲጋራ በሚያጨሱ ሰዎች አካባቢ የሚገኙ ህፃናት ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አዲስ የወጣ ጥናት አመላከተ። ጥናቱ እንዳመላከተው  ከሲጋራ የሚወጣው ጭስ በህጻናት የደም ቧንቧ ላይ ጉዳት ያደርሳል። ተመራማሪዎቹ ከ8 እስከ 18 ዓመት ዕድሜ መካከል…