የዳንኤል አራፕ ሞይ ብሄራዊ ቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ። ባለፈዉ ማክሰኞ በ95 ዓመታቸዉ ያረፉት የቀድሞዉ የኬንያ ፕሬዚዳንትን ዳንኤል አራፕ ሞይ ዛሬ ብሄራዊ ቀብር ሥነ ስርዓታቸው ተፈጽሟል። በቀብር ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች መሪዎች ተገኝተዋል። የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።…

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንንና አፋር ክልልን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች የሚጠፋው ህይወትና የሚደርሰው ጉዳይ እያሳሰበው እንደሆነ የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት አስታውቋል። “ደም አፋሳሽ ግጭቶች እንዳይደገሙ መንግሥት የህግ የበላይነትን ያስከብር” ብሏል ድርጅቱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር…

ያሳዝናል በርቀት የተማሩ ሰዎች በርቀት እያስተዳደሩ ነው። የብአዴን ባለስልጣናት ክልሉን አዲስ አበባ ተቀምጠው በርቀት ለመምራት እየሞከሩ ነው። ከሀምሌ 01/2011 ዓም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር በአውሮፕላን እየተመላለሱ በደሀ ህዝብ ገንዘብ እየቀለዱ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ። ለአየር ትኬት በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ…

የሱዳን የሽግግር መንግሥት የቀድሞውን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦመር አል ባሽርን ለዓለምቀፍ የወንጀል ችሎት ለማስረከብ ተስማምቷል። ዛሬ ስለ ውሳኔው ወሪ የተሰማው የሱዳን መንግሥትና የዳርፉር ክልል አማጽያን በደቡብ ሱዳን መዲና ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ ነው ተብሏል። የፍትህና የእኩልነት ንቅናቄ የተባለው የአማጽያን ድርጅት ተወካይ አሕመድ…

የሙያው ባለቤቶችና ተመራማሪዎች ታጋቾችን ማስለቀቅ ራሱን የቻለ ታላቅ ጥበብና ስልት ይጠይቃል ይላሉ። የአጋቾችን ስነልቡና ለመስረቅ፣ ለማለስለስ፣ ወዘተ አደራዳሪዎች ፈጽሞ ሊታሰቡ የማይችሉ የሚባሉ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ። የአጋቾቹን ፍቅረኛ ወይም እናት ወይም ሌላ ተወዳጅ የቤተሰብ አባል ወደ ዕገታው ቦታ በማምጣት በድምጽ ማጉያ…

የዚህች ሃገር ችግር የሴራ ፓለቲካ ነው። ጀዋር ሞሃመድ ዛሬ (ሰኞ) ለማየት የሚሰቀጥጥ አንድ ቪዲዮ ለጠፈ። በጣም አንጀት የሚበላ ጥቁርም ሆነ ነጭ ኦሮሞም ሆነ አማራ፤ የሰውን ልጅ እንደዛ በጭካኔ ማሰቃየት ከባድ የሰብዓዊነት ጥሰት ነው። የህግ ተጠያቂነት ደግሞ ግድ ነው፤ ግን ደግሞ…