ህዝበ ሙስሊሙ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን በረመዳን ወርም ተግባራዊ ማድረጉን እንዲቀጥል ተቀደሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ አሳሰቡ። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ በዚህ ሳምንት የሚጀመረውን የረመዳን ፆም አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል። ለተጨማሪ የተያያዘውን…

በምሥራቅ አማራ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የተለያዩ ምርቶችን በማምረትና በማከፋፈል ላይ ይገኛሉ። ዩኒቨርሲቲዎቹ እንደ የእጅ ንጽህና ፈሳሽ ምርቶችን በማምርት ላይ ቢሆኑም ከፍተኛ የግባዓት እጥረት ስላለባቸው በፈለጉት መጠንና ፍጥነት እየሰሩ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከሰቱ ይፋ በሆነበት ሰሞን መድኃኒት ቤቶች፣…

በደቡብ ሱዳን ዋናውን ተቃዋሚ ፓርቲ እየከዱ በፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ወደ ሚመራው ገዥው ፓርቲ የሚገቡት አባላት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። አንደኛው ተቃዋሚውን ፓርቲ የከዱ አባል የፓርቲውን መሪ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱን ሪያክ ማቻርን ፓርቲውን የቤተሰብ ርስታቸው አድርገውታል ብሏል። 

የደቡባዊ አፍሪካዊቱ ሀገር የሌሴቶ ጥምር መንግሥት በቅሌት የተጠመዱት ጠ/ሚ ቶማስ ታባኒ በአስቸኳይ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠየቀ። የ80 ዓመቱ ታባኔ ከሦስት ዓመታት በፊት የቀድሞዋ ባለቤታቸው ሊዮፖሎ ታባኔ ላይ በተፈረመው ግድያ እጃቸው አለበት ተብለው ከተወነጀሉ ወዲህ ከሥልጣን ይወረዱ የሚለው ግፊት እየበረታባቸው መጥታል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተገኘ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገለፀ ፡፡ የቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ ዋና ሳጅን ዳምጠው ሞላ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው ሚያዚያ 12 ቀን…

ኅብረተሰቡ ስለ ኮሮናቫይረስ ግንዛቤ ቢኖረውም ትግበራ ላይ ግን ብዙ እንደሚቀር አንዳንድ የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ለዚህ ማሳያ ያደረጉት ደግሞ የእንቅስቃሴ አገዳ መነሳቱን ተከትሎ በበዓል ገበያ የታየውን መዘናጋት ነው። አንድ የሚድያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ ደግሞ መንግሥት ከዚህ አንፃር ያለውን ክፍተት ለመሙላት አስገዳጅ…

በድሬዳዋ የኮሮናቫይረስ የነበረባቸው ሁለት ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ወደቤታቸው ሲመለሱ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሦስቱም ሰዎች ከጂቡቲ ተመልሰው በለይቶ ማቆያ ያሉ ናቸው።  ከጂቡቲ ተመልሰው በለይቶ ማቆያ የሚገኙ 574 ሰዎች በሙሉ የደም ናሙናቸው ተልኮ ውጤት እየተጠበቀ ነው…