246 ቢሊየን ብር ወጪ የወጣባቸው 16 የመንግስት ፕሮጀክቶች ተቋርጠዋል፤ ከ44 ቢሊየን ብር በላይ ብክነት ደርሷል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/201519

16 የመንግስት ፕሮጀክቶች አዋጪነት ጥናት ሳይደረግባቸው በመጀመራቸው 246 ቢሊየን ብር ወጪ ከወጣባቸው በኋላ መቋረጣቸውን የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ።የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የመንግስት ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን በተመለከተ ከ2008 እስከ 2010 እና የ2011 በጀት ዓመት ባከናወነው የመንግስት ፕሮጀክቶች የክዋኔ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የፕሮጀክቶቹ መቋረጥን ተመልክቷል፡፡
ፕሮጀክቶቹ የተሟላ የጥናት ሰነድ ቅድመ ዝግጅት እና የዲዛይን ጥናት ሳይደረግባቸው በመተግበራው ለመቋረጣቸው ምክንያት መሆኑንም ሰምተናል፡፡ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ወጪ ከወጣባቸው በኋላ መቋረጣቸው ውስን የሆነውን የመንግስት ሃብት እንዲባክን ከማድረጉም በላይ ከፕሮጀክቶቹ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ የማህበረሰብ ክፍሎችንም ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጉንም ተቋሙ ገልጿል፡፡

በአስፈፃሚ መ/ቤቶች የሚቀርቡ የመንግስት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት እና የቅድመ ትግበራ ግምገማ ስራ ባለመከናወኑ በ290 ፕሮጀክቶች ተደጋጋሚ የጊዜ እና የበጀት ክለሳ በመደረጉ ምክንያት ከ 44 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ያስከተለ መሆኑ እና መባከኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ከዚህ ውስጥም በቀድሞው የውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ስር የነበሩ 18 ፕሮጀክቶች ከ32 ቢሊየን ብር በላይ ወይም 72 በመቶውን የሚይዙ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም በተያዘላቸው ጊዜ ያልተጠናቀቀቁ 369 ፕሮጀክቶችም መኖራቸውም በኦዲት ግኝቱ ማረጋገጡን ተቋሙ አስታውቋል፡፡ተጨማሪ 54 ፕሮጀክቶችም ቢሆን በበጀት ክለሳ ምክንያት ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ማስከተላቸው ተነግሯል፡፡
በአስፈፃሚ መ/ቤቶች የሚቀርቡ የመንግስት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት እና የቅድመ ትግበራ ግምገማ ስራ ባለመከናወኑ ፕሮጀክቶች ተደጋጋሚ የጊዜ እና የበጀት ክለሳ በመደረጉ ምክንያት ሀገሪቱ በቢሉዮኖች ለሚቆጠር ወጪ እየተዳረገች መሆኑን ፣ ፕሮጀክቶች በመቶ ሚሉዮኖች ወጪ ከወጣባቸው በኋላ እየተቋረጡ መሆናቸው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.