32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ

Source: https://fanabc.com/2019/02/32%E1%8A%9B%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%88%85%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8C%89%E1%89%A3%E1%8A%A4-%E1%89%B0%E1%8C%A0/

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ማምሻውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

በስደተኞች፣ ከስደት ተመላሾች እና በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ጉባኤ በአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በመስማማት ተጠናቋል።

የወቅቱ የህብረቱ ሊቀ መንበር በመሆን የተመረጡት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አል ሲ ሲ፥ በህብረቱ አባል ሃገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ውህደት ሊኖር ይገባል ብለዋል።

ጉባኤው በዛሬው ውሎው በአህጉሪቱ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በስፋት መክሯል።

በዚህም ከሰላምና ፀጥታ ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የፀረ ሽብር ዘመቻውን ማጠናከርና አካታች ልማትን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም የወጣት ሴቶችን ስጋት መቅረፍና ሴቶችን ወደ አመራርነት ከማምጣት አንጻር ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባልም ተብሏል።

ህብረቱም በአህጉሪቱ ያለውን የሰላምና የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ ከመንግስታቱ ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራትም ተስማምቷል።

 

 

በስላባት ማናዬ

 

 

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.