43 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ ከ1 ሺህ በላይ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ተሰማርተዋል

43 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ ከ1 ሺህ በላይ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ተሰማርተዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ግንባታቸው ተጠናቀው ወደ ስራ የገቡ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ 1 ሺህ 564 የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መሰማራታቸው ተገለፀ።
 
በዚህም የቻይና ኩባንያዎች በፕሮጀክቶች የቁጥር መጠንም ሆነ ባፈሰሱት መዋዕለ ነዋይ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ቀዳሚዎቹ እንደሆኑ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።
 
እነዚህ የቻይና ኩባንያዎቹ ከፈረንጆቹ 1998 እስከ ባለፈው የፈረንጆቹ መጋቢት ወር 2020 ድረስ የተመዘገቡ መሆናቸውን በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መኮንን ሀይሉ ለሺንዋ ተናግረዋል።
ከ1 ሺህ 564 ኩባንያዎቹ መካከል 987ቱ ስራ ሲጀምሩ፥ 186ቱ ደግሞ በትግበራ ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው ብለዋል፡፡
 
ቀሪዎቹ 391 ደግሞ በቅድመ ትግበራ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
 
ከአጠቃላይ ፕሮጀክቶቹ ውስጥ 1 ሺህ 133 ፕሮጀክቶች በማምረቻው ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆን ሌሎች በሆቴል፣ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኮሙዩኒኬሽ እና ግንባታ ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው።
 
እነዚህ ፕሮጀክቶች 43 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ወይም 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ሀብት ያስመዘገቡ መሆናቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።

The post 43 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ ከ1 ሺህ በላይ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ተሰማርተዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply