43 ክላሽ ሸንኮቭና 1 ሺህ 300 ጥይቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታወቀ

Source: https://fanabc.com/2019/02/43-%E1%8A%AD%E1%88%8B%E1%88%BD-%E1%88%B8%E1%8A%95%E1%8A%AE%E1%89%AD%E1%8A%93-1-%E1%88%BA%E1%88%85-300-%E1%8C%A5/

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያና 1 ሺህ 300 ጥይቶች በቁጥር ስር ማዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታወቀ።

የጦር መሳሪያዎቹን ከጋምቤላ ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ በኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ በማስገባት ላይ እያለ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፥ የመኪናው አሽከርካሪም በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።

ምንጭ፦ አብመድ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.