90 ሚሊዮን ዶላር የወጣበትና ቆሞ የቀረው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፖርክ

Source: http://welkait.com/?p=10947
Print Friendly, PDF & Email

(ልሳነ-ዐማራ ፤ ህዳር 5 / 2010 ዓ.ም)

በ90 ሚሊየን ዶላር፤ የተገነባው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፖርክ ከተመረቀ በኃላ እስካሁን ስራ እንዳልጀመረ ተገለፀ ።

በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች በብድር ገንዘብ ከተገነቡት የኢንዱስትሪ ፖርኮች መካከል፤ በ90 ሚሊየን ዶላር ወይም 2.4 ቢሊየን ብር ገደማ ወጪ ተደርጎበት ሀምሌ 1/2009 ዓ.ም የተመረቀው የኮንቦልቻ ኢንዱስትሪ ፖርክ አንዱ ነው። ይህ በ75 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ፤ ኢንዱስትሪ ፖርክ ሲገነባ ፤ እጅግ በርካታ አርሷደሮች ያለበቂ ካሳ አፈናቅሏል። ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ፤ ለአገልግሎት በማዋል ለበርካታ ስራ አጥ ወጣቶች ፣ ከሳኡዲ ተመላሽ ስደተኞች እንዲሁም መሬታቸውን ለተነጠቁ አርሷደር ቤተሠቦች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ተስፋ ተሠጥቶ እንደነበር ይታወቃል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገመቹ ፤ “… የኮምበልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ የተካሄደው በ75 ሄክታር መሬት ላይ ነው። የፓርኩ ዋና ትኩረትም ጨርቃ ጨርቅና አልባሳትን በማምረት የወጭ ንግድን ማጠናከር ነው ። በመጀመሪያው ምዕራፍ በተገነቡት ዘጠኝ ሼዶች ለ20 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ሲሆን ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኩ በአፋጣኝ ስራ ለመጀመር የአሜሪካ፣ የኮሪያና የጣሊያን ኩባንያዎች ገብተው ለመስራት ጥያቄ አቅርበዋል።” ፤ ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን ፤ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፤ ባለፉት አራት ወራት ፤ “…በፖርኩ ስራ ለመጀመር ጥያቄ አቅርበው ፤ የግንባታውን መጠናቀቅ እየጠበቁ ነው።” ፤ የተባሉት ኩባንያዎች እስካሁን በአካባቢው ” ዝር” አለማለታቸውን ነዋሪዎች አረጋግጠዋል። ይህን ተከትሎ የስራ ዕድል እናገኛለን በማለት ፤ ተስፋ ያደረጉ ስራ አጦችና የአካባቢው ማህበረሰቦች ፤ ” መንግስት ቃል የሚገባው ከንቱ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘትና በደመነፍስ ተመርቶ እንጂ በትክክል በታቀደ የስራ አፈፃፀም የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት አይደለም። ” ሲሉ ፤ ቅሬታቸውን ለልሳነ-አማራ ሪፖርተር ተናግረዋል።

90 ሚሊዮን ዶላር የወጣበትና ቆሞ የቀረው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፖርክ

Share this post

One thought on “90 ሚሊዮን ዶላር የወጣበትና ቆሞ የቀረው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፖርክ

  1. ይሄ ሁሉ ስራ የነ አርከበ እና ሽመልስ ክንዴ ስራ ነው አርከበ የጁን አገኘ ሌላውንም እንጠብቃለን
    ሃዋሳ ኦሞ ኩራዝ ኢነርጂ ሜትር ምኑ ቅጡ……

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.