ትምህርት ለማስጀመር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) በኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስጀመር አገዛዙ በሀገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ተነገረ። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የዘር ልዩነት ያመጣውን አገዛዝ በመቃወም ድምጻቸውን በማሰማታቸው በአጋዚ ሃይሎች በመደብደባቸው ግቢውን እየጣሉ ወደ ቤታቸው አምርተዋል። በአማራ ክልል ባሉ…
ተማሪዎች አደባባይ በመውጣት ሀዘናቸውን ገለጹ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የጨለንቆውን ጭፍጨፋ በማውገዝ የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚማሩ ተማሪዎች አደባባይ በመውጣት ሀዘናቸውን ገለጹ። በተለይ በወለጋ ነቀምት ጥቁር ልብስ የለበሱት ተማሪዎች በሰልፍ ወጥተው ግድያውን በማውገዝ ላለቁት ወገኖች ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ከአንድ ቤተሰብ 5 ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 18 ሰዎች የተገደሉበት…
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሽግግር ሰነድ አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የአውሮፓ ፓርላማ በጠራውና ኢትዮጵያን በተመለከተው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሽግግር ሰነድ ማቅረቡ ተገለጸ። የሽግግር ሰነዱ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት አገዛዝ ከወደቀ በኋላ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሽግግር ስርዓት የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል። በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ…
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከነውዝግቡ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መቀጠሉ ታወቀ። የደህንነቱ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዲፈርስ ጠይቀዋል። ብአዴንና ኦህዴድ ራሳችሁን አጥሩ በሚል በሕወሃት የቀረበው ሃሳብም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህ ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለው ስብሰባ…

እነሆ ራሳቸው በጠሩዋቸው ጉባዔዎችና ኮንፍረንሶች ላይ ሁሉ በተደጋጋሚ ተነግረዋል አልሰሙም፤ ተመክረዋልም አልታረሙም። እኒህም የኢትዮጵያ ገዢዎች የኢህአዴጋውያን አዛዦች የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ህወሃታውያን ናቸው። ማስረጃ ቢባል ማርሻል መለስ ከመራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉባዔ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ የዘለቁት መሰል ጉባዔዎች…

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ነፍጥ አንጋቢዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት የጨለንቆ ወገኖች በነቀምቴና በአዳማ ተማሪዎች መታሰቢያ አድርገዋል። የቢቢሲ የኦሮሚኛ ዘገባ እንዳስረዳው ከአንድ ቤት አምስት ሞተዋል። (ፎቶዎቹ ከማህበራዊ ድረገጾች የተገኙ ናቸው) በነቀምቴ ወለጋ አዳማ ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ እድሜልክ እስራት ተፈረደባቸው ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ  እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት…
ስኳር ኮርፖሬሽን ከውጭ ገዝቶ ካስመጣው 2 መርከብ ስኳር ውስጥ 3 ሺህ 777 ኩንታሉ “የገባበት ጠፋ”!!

የስኳሩ ጉዳይ… የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በመተሃራ ተበላሽቷል ተብሎ ስለተቀበረው ስኳር ማስረጃ አላገኘሁም አለ… ስኳር ኮርፖሬሽን በውጭ ምንዛሬ ገዝቶ ወደ ሐገር ካስገበው 2 መርከብ ስኳር 3 ሺህ 777 ኩንታሉን ተበላሽቷል ብሎ ቀብሮታል ተብሏል፡፡ የዓይን እማኞች ጭምር አሉኝ ቢልም ስለመቅበሩ…

(ጠበቃ አለልኝ ምህረቱ) ~ሕዝቡ አማራ ነኝ ካለ አማራ ነው ጥያቄው እዚህ ላይ ያበቃል። ግላዊ ማንነቱን ሌላ ሰው እንዲወሥንለት መጠበቅ የለበትም! ~የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ አዲስ ማንነት እንዲሰጣቸው ሣይሆን የነበረውን ማንነታቸው ስለተነጠቁ የተወሰደ ማንነታቸው እንዲመለስላቸው ብቻ ነው። በመሆኑም የዋልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ እና…
የእነ ነጋ የኔነው የክስ መቃወሚያ

~ የአንዳንዳችን ላይ የቀረበው ማስረጃ እኛ ያልሰጠነው በመርማሪ ፖሊስ ተዘጋጅቶ በማሠቃያ ክፍል ውስጥ ሆነን ሣናውቀው እና ሣይነበብልን በግዴታ ውስጥ ሆነን የፈረምነው በመሆኑ ከመፈረማችን በፊትም የሕግ ምክር አገልግሎት እንዳናገኝ ተገድበን እና ተገድደን የፈርምነበት እንጅ ወደን እና ፈቀደን ያልሰጠነው ቃል ስለሆነ አሁን…

ሃሳብ ወለድ የኢትዮጵያዊያን ዉይይቶች (ተስፋዬ ደምመላሽ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕወሓት አገዛዝ ጋር ዛሬ የሚያኪያሂዳቸዉ አካባባዊና ታክቲካዊ ትግሎች በምን መንገድ ነዉ ወደ ዘላቂ አገር አቀፍ ስልታዊ ንቅናቄ የሚሸጋገሩት? ከጽንሱም መሠረቱም ብልሹ የሆነዉና ዛሬ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተቀባይነቱ ጨርሶ የተሟጠጠበት ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ራሱን…
ኢትዮጵያ ወይስ ኩሽ? –  ጌታቸው ኃይሌ

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ አንድ ሰሞን “የጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በሪቨረንድ በንቲ ቴሶ ኡጁሉ ተጽዕኖ የኢትዮጵያን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰርዛ በኩሽ ለውጣዋለች” የሚል ወሬ ተናፍሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን አበሳጭቶ ነበር። ብዙ ተቃውሞም ተጽፏል። ይኼ ተጨማሪ ማብራሪያ ነው። ከመጀመሪያው…

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) የጨለንቆውን ጭፍጨፋ በመቃወም በመላው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። ተቃውሞው አዲስ አባባ ዙሪያ መድረሱንም ለማወቅ ተችሏል። በወለጋ ጊምቢና ነጆ፣ በጂማ በአጋሮና በአብዛኛው የምስራቅ ሀረርጌ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። በሞያሌ በአጋዚና በህዝቡ መሃል ግጭት ተፈጥሯል። በአምቦ የተገደሉ…
ህዝባዊው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። በአይከል ከተማ ህዝቡ አደባባይ በመውጣት የህወሃትን አገዛዝ ማውገዙ ታውቋል። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። ህወሀት ከስልጣን እንዲወርድ ተማሪዎቹ ጠይቀዋል። በጎንደር ዩኒቨርስቲ ዛሬም ትምህርት አልተጀመረም። አንድ የመንግስት ተሸከርካሪ…
ዚምባቡዌ መንግስቱ ሃይለማርያምን አሳልፌ አልሰጥም አለች

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) ዚምባቡዌ የቀድሞ የኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሐይለማርያምን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች። የዚምባቡዌ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባለፈው ወር ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ሀገሪቱ መንግስቱ ሃይለማርያምን ወደ ሀገራቸው እንድትሰድ በመጎትጎት ላይ ናቸው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም አጋርና ወዳጅ የሆኑት…