ደንጋራው፣ ከርካሚው፣ ሲፊኒክሱ፣ ህዝብ አልቦው “ብአዴን”

(መስከረም አበራ) አምባገነንነት የሃገራችን ገዥዎች መለያ እንደሆነው ሁሉ የእርስበርስ መቆራቆስ ደግሞ የተቃውሞውን ፖለቲካ የተጣባ ክፉ ደዌ ነው፡፡ በተቃውሞ ፖለቲካ ጀማሪዎቹ መኢሶን እና ኢህአፓ መሃከል የነበረው የጎንዮሽ ልፊያ የዚህ አይነተኛ መገለጫ ነው፡፡ በኢህአፓ ውስጠ-ፓርቲ ውስጥ የነበረው እርስበርስ መበላላት ትልቁን ዳቦ (ኢህአፓን)…

በጸጥታ እቅድ ስም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ የቁም እስር ተደነገገለት። አስቸኳይ ጥሪ ለአገር ልአላዊነት ለቆምን ብቻ ሳንሆን የኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ ማወቅ ያለብን ጉዳይ። ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ከዚች በታች ያለችው አጭር ማሳሰቢያዬን ተመልክታችሁ ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ ከዚህ ቀጥሎ በምታዩት አረስት “ወቅታዊ የሃገራችን ሁኔታ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ጋብ ብሎ የነበረው በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር አካባቢ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ። በሞያሌ አቅራቢያ ቦርቦር በተባለው አካባቢ በተቀሰቀሰው በዚሁ ግጭት ከሁለቱ ወገኖች 27 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የህወሃት ልዩ ኮማንዶ በአካባቢው ከገባ በኋላ ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች በግድያው ላይ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)በግብጽ ሳይናይ ግዛት በአንድ መስጊድ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 235 ሰዎች ሲገደሉ 130 ሰዎች ቆስለዋል። የሟቾቹም ሆነ በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል መረጃዎች ጠቁመዋል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሶስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀንም አውጀዋል። እስካሁንም ለጥቃቱ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ሮበርት ሙጋቤን የተኩት አዲሱ የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ኤምርሰን ናንጋግዋ ቃለ መሃላ ፈጸሙ። ቀደም ሲል በሮበርት ሙጋቤ ከምክትል ፕሬዝዳንትነት የተባረሩት ኤመርሰን ናንጋግዋ በሕዝብ ግፊት ሕገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ የሀገሪቱ መሪ ሆነዋል። ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ በዚምባቡዌ ዲሞክራሲያዊ ስረአት እንደሚያሰፍኑና…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)የሀዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ መምህራን ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተገለጸ። መምህራንን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በደቡብ ክልል መንግስት የወጣው መመሪያ ተፈጻሚ ሳይሆን ቤት እንዳገኘን ተደርጎ ሪፖርት መቅረቡና በመገናኛ ብዙሃን መነገሩ አስቆጥቶናል ያሉት መምህራን የአንድ ቀን ስራ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ከሞያሌ በሳምንቱ መጀመሪያ የተሰወሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መክዳታቸውን ምንጮች ለኢሳት አረጋገጡ። የከዱት የሰራዊቱ አባላት ቁጥርም 38 እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል። እነሱን ለመፈለግ የወጣው ሃይልም አለመመለሱ ታውቋል። ሆኖም ለአሰሳ በወጣው ሃይል ውስጥ በተፈጠረ ውዝግብ አንድ ወታደር ሲገደል አንድ መቁሰሉን ምንጮቹ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በመከላከያ አመራር ላይ ከፍተኛ ብወዛ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ። ብወዛው በተለይ የኦሮሞና አማራ ተወላጆች ላይ የተነጣጠረ መሆኑንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በጄኔራል መኮንኖች አካባቢ አመራሩ በሕወሃት ጄኔራሎች በመያዙ ብወዛው ከዚያ በመለስ ባለው የስልጣን መዋቅር…
“በአማራነታችን እንሞታለን፣ አማራነታን አትፍቁትም” – በእስር ላይ የሚገኙ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች

(አያሌ መንበር) አማራ ነን በማለታቸው ብቻ “ወንጀለኛ” ተብለው ተከሰው እየተሰቃዩ የሚገኙትን የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች የክስ ሂደትን ለመመልከት የሄደው ወጣት የእነርሱን ንግግር በማስቀደም እና ፎቶዎችንም በማያየዝ የላከልኝ መልዕክት ነው። ወንድሜ እንዲህ ሲል ይጀምራል፦ “ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የልደታ 4ኛ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010)አመታዊው የምስጋና ቀን/ታንክስ ጊቪንግ/ዛሬ በአሜሪካኖች ዘንድ ተከብሮ ዋለ። በአሜሪካ የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ሁኔታና አቅም በፈቀደ መጠን በአሉን ያከብራሉ። በአሜሪካውያኑ ዘንድ በያመቱ በህዳር ወር 4ኛው ሀሙስ ላይ የሚከበረው የምስጋና ቀን/Thanksgiving/ ምስጋና የሚሰጥበትና ቤተሰብና ጓደኛ ሰብሰብ ብሎ የሚያከብረው ቀን ነው።…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010)የንግድ አጋሩን ለማስገደል ተንቀሳቅሷል በሚል የተወነጀለው ኢትዮጵያዊ በካናዳ ዊኒ ፔግ የ5 አመት አስራት ተፈረደበት። በፖለቲካ ጥገኝነት በካናዳ የሚኖረው አቶ አማረ ገብሩ እስራቱን ሲጨርስ ከሀገር እንደሚባረርም ይፋ ሆኗል። ይህን ቤተሰቡን ያስደነገጠውን የማባረር ርምጃ ለማስቀረትም ጠበቆች እስራቱን በይግባኝ ለማስቀነስ በመሯሯጥ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010) የአባይ ጉዳይ ለእኛም የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለጹ። ቃል አቀባዩ አቶ መለስ አለም የአባይ ግድብን በተመለከተ ከግብጽ ጋር ውጥረት መከሰቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ኢትዮጵያ በራሷ አቅም አባይን መገደቧን ትቀጥላለች።…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010) የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሆቴሎችና በልዩ ልዩ ቦታዎች አገልግሎት በሚሰጡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የአሜሪካ የኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን ርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ። በዋናነት በአሰሪዎቹ ላይ ያነጣጠረውና ተቀጣሪዎቹንም የማይተወው ርምጃ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ መመስረትንም ይጨምራል። ተቀጣሪዎቹ ደግሞ በሌላ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010) ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ባህርዳር ላይ የተገደሉት የፌደራል ፖሊስ የሰሜን ምዕራብ አዛዥ ኮማንደር ደሳለኝ ልጃለም የቀብር ስነ ስርአት ዛሬ ተፈጸመ። አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ለኮማንደሩ ግድያ ሃላፊነት መውሰዱን አስታውቋል። የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊም ኮማንደሩ መሞታቸውን…
“ይህ ዘርን ማዕከል ያደረገ ጥቃት አድሃሪ ነው። በጣም መጥፎ ነው።” – ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት

ቱጃሩና የራያ ቢራ ፋብሪካ ባለቤት የሆነው ጀኔራል አበበ ተክለሃይማኖት ሰንደቅ ለተባለ በአዲስ አበባ ለሚገኝ ጋዜጣ በሰጠው ቃለ መጠየቅ “ይህ ዘርን ማዕከል ያደረገ ጥቃት አድሃሪ ነው። በጣም መጥፎ ነው።” በማለት ተናግሯል። ጀንራል አበበ ታዲያ እንደዚያ ከሆነ ለምን ነው እናንተ የመሰረታችሁት የትግራይ…