በኢትዮጵያውያን የፌስ ቡክ እና ትዊተር ተጠቃሚዎች ዘንድ ከሳምንት ሳምንት የማይበርድ አንድ አጀንዳ ቢኖር የብሔር እና የክልል ጉዳይ ነው፡፡ መልኩን እየቀያየረ እና በሰሞነኛ ጉዳዮች ላይ እየተንተራሰ የሚያወዛግበው ይህ አጀንዳ በዚህ ሳምንትም ከትግራይ ክልል ጋር በተገናኘ መወያያ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የነገሩ መነሻ በመቀለ…

(ሸክም የበዛበት ትውልድ፡2009 እና የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ) በኹለንተናዊ የማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የዓለምም ኾነ የሀገራችን ትንታኔዎች ውስጥ ሕዝብ የሚለው ቃል እጅግ ተዘውትረው ከሚነሱ ቃላት መሐከል ዋነኛውና የኹሉ ነገር ማጠንጠኛ ኾኖ እናገኘዋለን፡፡ እንግሊዘኛው መዝገበ ቃላት ሕዝብ (people) ማለት”The members of…

Washington Update – January 31, 2018 House leadership was briefed on Tuesday about the situation in Ethiopia by Ethiopian /Americans activists.   The meeting was organized in coordination with Congressman Chris Smith’s office and the Majority Leader office for the House leadership…
ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) ወቅታዊ መግለጫ

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) ወቅታዊ መግለጫ በአማራና በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በመንግስትና በንግድ ስራዎች ሽፋን የሚንቀሳቀሱ የህወሃት ሰላዮች በመላ ሀገሪቱ ሲካሄዱ የነበሩና የሚካሄዱ ህወሃታዊ የዘር ፍጅቶችን በማቀነባበር ሴራ ቀንደኛ ተጠያቂዎች እስከሆኑ ድረስ እነዚህን ፀረ ሃገርና ፀረ ህዝብ የህወሃት ሎሌ ሰላዮች በመመንጠር…

ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉየኦሮሚያ ተወላጆች የሚሆኑ ሰፋፊ ሄክታሮችን ከየትም ብለው በተቻለው ፍጥነትእንዲያዘጋጁ ለአዲስ አበባ የአስሩም ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮኃላፊዎች ታዘዙ፡፡ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ለአስሩም ክፍለከተሞች በተበተነ ደብዳቤ ነው ይህ ትዕዛዝ የተላለፈው፡፡ ሰፋፊ መሬቶቹ የሚዘጋጁትከወራት በፊት ከሶማሌ ክልል የድንበርና የብሔር ግጭትን ተከትሎ የተፈናቀሉ በሺዎችየሚቆጠሩ የኦሮሚያ ተወላጆችን በቋሚነት ለማስፈር ነው ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች እንዲሰፍሩ የሚደረጉት ተፈናቃዮች ትክክለኛ ቁጥር በውልባይታወቅም ወደ ሶማሌ ክልል ከመሄዳቸው በፊት በአዲስ አበባ ኗሪ እንደነበሩ መረጃማቅረብ የቻሉ ተወላጆች ብቻ የፊንፊኔ ቋሚ ነዋሪ እንዲሆኑ እንደሚደረግ በመሬት ዝግጅቱ ተሳታፊ የሆኑ አንድ የድርጅት አባል ትናንት ማምሻውን ለዋዜማተናግረዋል፡፡ ለነዚህ ተፈናቃዮች መጠለያ የሚውል ቦታ እንዲያቀርቡ ከሚጠበቅባቸው ክፍለ ከተሞች መሐል አቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራንዮና የቦሌ ክፍለ ከተሞችበቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ ክፍለ ከተሞቹ እያንዳንዳቸው ከ15 ሄክታር ያላነሰ መሬት እንዲያፈላልጉ ነው የተነገራቸው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኮልፌ ቀራንዮ አሸዋ ሜዳ አቅራቢያ በሚገኙ ሰፈሮች ለተፈናቃዮች ቦታ ለማዘጋጀት በተደረገ እንቅስቃሴ ከአካባቢው ቀደምትነዋሪዎች ጋር መጠነኛ ግጭት ተፈጥሮ የሰው ሕይወት መጥፋቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በመልካሙ ጊዜ ከገበሬ ቦታ ገዝተው ይዞታቸውን ወደ ሕጋዊነት ለማስቀየር ሲጠባበቁ የነበሩ እነዚህ ዜጎች ይዞታቸው ለተፈናቃዮች እንዲውል መታሰቡ ጭራሽያልጠበቁት ዱብዕዳ ኾኖባቸዋል፡፡ ይህን እንቅስቃሴ ለመግታት ያደረጉት ጥረትም የጸጥታ ኃይሎችን ያሳተፈ ግጭት እንዲያስተናግድ አድርጎ ነበር፡፡ 1400 ኪሎ ሜትሮችን የሚጋሩት የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ሰፊ የቆዳ ስፋት ያላቸው ክልሎች ሲሆኑ የድንበር ቀበሌዎቻቸውን አከላለል በተመለከተ በጥቅምት1997 ሕዝበ ውሳኔ አድርገው ነበር፡፡ ኾኖም ሕዝበ ውሳኔው ለአስር ዓመታት ወደ መሬት ሳይወርድ ቆይቷል፡፡ በ27 ዓመታት የኢህአዴግ አመራር ታሪክ እጅግ በርካታ ሕዝቦችን ለሞትና መፈናቀል የዳረገው ይህ ውዝግብ በትንሹ ግማሽ ሚሊዮን ዜጎችን ከቀያቸውአሸሽቷቸዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ በአጎራባች ከተሞች፣ በመስጊድና አብያተ ክርስቲያን፣ በጤና ጣቢያዎች፣ በጦር ካምፖች፣ በስቴዲየሞች፣ በግል ኮሌጆችና በግለሰብ ቤቶችጭምር ተጠልለው ይገኛሉ፡፡  የኦሮሚያ ክልል ባለሀብት የሆኑት አቶ ድንቁ ደያስ የተወሰኑ ተፈናቃዮችን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት የሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ቅጥርውስጥ በማቆየትና ከኪሳቸው 12 ሚሊዮን ብር በመለገስ አጋርነታቸውን አሳይተው ነበር፡፡ በርካታ ተፈናቃዮች ዛሬም ድረስ የተጠለሉት በላሜራ በተሠሩ ትልልቅመጋዘኖች መሆኑ ቀን ቀን ለከፍተኛ ሙቀት፣ ምሽት ለከፍተኛ ቅዝቃዜ ተጋልጠው አስቸጋሪ ሕይወት እየገፉ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ የተፈናቃዮች ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ አስተባባሪ ዶክተር አበራ ደሬሳ ከሁለት ወራት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ‹‹የተፈናቃዮች የኋላ ታሪክና የወደፊትፍላጎታቸው እየተጠና›› በተለያዩ ቦታዎች እንዲሰፈርሩ ጠቁመው ነበር፡፡ ምናልባት በርካታ ነዋሪዎችን አዲስ አበባ በቋሚነት የማስፈሩ ሐሳብ እየተተገበረ ያለው ይህንጥናት ተከትሎ በተደረሰ ዉሳኔ ሳይሆን እንዳልቀረ የሚገምቱ አሉ፡፡ ዶክተሩ በወቅቱ ለዚሁ አለም አቀፍ የዜና አውታር በሰጡት ማብራሪያ ‹‹በንግድና ከተሞች አካባቢየሚሰሩ ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳደሩ ሰዎችን በፊንፊኔ ዙርያ በሚገኙ ልዩ ዞኖች ለማስፈር ዝግጅት ተጠናቋል›› ብለው ነበር፡፡ ኾኖም አስተባባሪው በአዲስአበባ  ዙርያ እንጂ በአዲስ አበባ ውስጥ የኦሮሚያ ተፈናቃዮችን በቋሚነት ስለማስፈር በወቅቱ ያሉት ነገር አልነበረም፡፡ በተመሳሳይ ኑሯቸውን ግብርና ላይ ያደረጉተፈናቃዮችም ወደተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ለመደልደል የእርሻ መሬት እየተለየ ቆይቷል፡፡ በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ልዩ ዞኖችና በአዲስ አበባ የሚሰፍሩት ከሶማሊ ክልል የተፈናቀሉት ብቻ እንደሚሆኑ፣ ነገር ግን ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ በሂደት በአጭርጊዜ ውስጥ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እንደሚደረግም ታውቋል፡፡ ይህ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስን ያስከተለን የድንበርና የብሔር ግጭት ተከትሎ ከፍተኛና ተከታታይ የገቢ ማሰባሰቢያ ጥረቶች መደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን የኦሮሚያተወላጅ ባለሐብቶችን፣ ሙዚቀኞችንና  ስመ ጥር አትሌቶችን ጨምሮ በተደረገ ርብርብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሎ ነበር፡፡ኾኖም ከችግሩ ስፋት አንጻር ገቢው ችግሩን ለመቅረፍ ቀርቶ ለማቃለል እንኳ የሚተርፍ አልሆነም፡፡ የድንበር ቀውሱን ተከትሎ በተሠራ አንድ ጥናት ከኦሮሚያ ተፈናቃዮች 97 በመቶ የሚሆኑት ከደኅንነት ሥጋት ጋር በተያያዘ ወደ ሶማሌ ክልል ለመመለስ ፈጽሞ ፍላጎትእንደሌላቸው ታውቋል፡፡ ያም ሆኖ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ግጭቱን ተከትሎ ሁሉም የኦሮሚያ ተፈናቃዮቹ ወደ ክልላቸው ሶማሌ እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጋቸውይታወሳል፡፡ በመኢሶ፣ በቦርደዴ፣ በአርሲ፣ በሞያሌ ቦረና፣ በምሥራቅ ሐረርጌ ኦሮሞዎችና አጎራባች የሶማሌ ተወላጆች፣ ከተፈጥሮ ሀብትና የግጦሽ መሬት ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞግጭትን ሲያስተናግዱ የቆዩ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ግጭቶቹ ፖለቲካዊ መልክ እየያዙ በመምጣታቸው ሰፊ ሰብአዊ ጥፋት እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ – ዋዜማ

ከላል ይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል ለቤተ- ጎለጎታና ቤተ -ሚካኤል ቤተ መቅደሶች እድሳት ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱ በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን እና ጥገናውን በሚያካሂደው ወርልድ ሄሪቴጅ ፈንድ በዛሬው እለት በላል ይበላ ከተማ ተፈርሟል። ሁለቱ ቤተ-መቅደሶች በረጅም እድሜ አገልግሎት…

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለመከላከያሰራዊት አባላት ወታደራዊ ማዕረጎች ሰጡ። የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት መግለጫ መሰረትም፦ የብርጋዴር ጀነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው 1. ኮሎኔል ፍሰሃ ስንታየሁ ዕምሩ 2. ኮሎኔል አስረሴ አያሌው ተገኘ 3. ኮሎኔል ደዲ አስፋው አያኔ 4. ኮሎኔል ዓለማየሁ ወልዴ ጅሎ 5.…

ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች 15 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) አስታወቀ፡፡ ካቢኔው ዛሬ ባወጣው መግለጫ በወልዲያ ከተማ በጥምቀት ዋዜማ በተቀሰቀሰው ግጭት “የተፈጸመው የሰው ግድያ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም” ብሏል፡፡  …

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ግብፅ የተቋረጠው ድርድር ይቀጥል ዘንድ አዲስ መፍትሄን የያዘ ምክረ ሃሳብ ይፋ አድርገው ነበር። ይህን ትልቅ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው ምክረ ሃሳብ ግብፅ “ገለልተኛ” ያለችውን የዓለም ባንክ በመካከላቸው ገብቶ እንዲያግባባ የሚጠይቅ ነው።…

አጭር የምስል መግለጫሊቨርፑል ከቶተንሃምአዲስ የሚመስለው የአርሴናል አጥቂ መስመር በመጪው ቅዳሜ ከኤቨርተን ጋር በሚደረገው ጨዋታ የመጀመሪያ ተሳትፎ ያደርጋል። ግን የቀድሞ አጥቂያቸው መነጋገሪያ ይሆን ይሆን?የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን “ቲዮ ዋልኮት ለአዲሱ ክለቡ ሁለት ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ ከቀድሞ ክለቡ ጋር የሚያደርገውን…
የማዕረግ ሹመትና ቀውሱ! ( አለበል አማረ )

የማዕረግ ሹመትና ቀውሱ! ( አለበል አማረ ) ዛሬ የህወሓት ልሳን የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በድምሩ ለ61 ትግሬወች ወይም ለህወሓት ታዛዦች በዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በኩል የጀኔራል መኮነንነት ማዕረግ መሰጠቱን ነግሮናል። እንደሚታወቀው የጀኔራል መኮነንነት ማዕረጉ የሚወሰነው በኢታማዦር ሹም ሁኖ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ፕሬዚዳንቱ…